Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

"የትግራይ ህዝብና መንግስት በራሳቸው ላይ እንዲደርስ የማይፈልጉት ነገር፣ በሌሎች ህዝቦችም ላይ እንዲደርስ ከቶም አይመኙም፣ አይፈቅዱም።" ፕረ. ደብረፅዮን

Post by sarcasm » 08 Nov 2021, 11:26

አሁን በውሸትና በቅጥፈት የሚቀየር ነገር የለም፣ ፋሽሽት ቡድኑም እንደሌሎች ሁሉ አምባገነኖች ስርአተ ቀብሩ በቅርቡ ይፈፀማል።
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~


የአሃዳዊው ስርአት ሌጋሲ አስቀጣይና ወራሽ ፋሽሽትው የአቢይ አሕመድ ቡድን፣ የውጭ ሀይላት እና ቁጥር ስፍር የሌለው የመሳርያ ጋጋታ በማሰለፍ እንደ ህዝብ ሊያጠፋን የቻለውን ያህል የተንቀሳቀሰ ቢሆንም፣ እንደ ህዝብ በከፍተኛ ብሄራዊ ጀግንነትና ፅናት ታግለን፣ ሁሉም ከበባዎች በጣጥሰን የጠላቶቻችን ዕድሜ ለማሳጠር እና ለመጨረሻ ጊዜ ለመቅበር፣ በመጨረሻ ምዕራፍ ላይ እንገኛለን። አሁን በጀግናውና ህዝባዊ ሰራዊታችን ፊት ላይ ቆሞ መዋጋት የሚችል አንዳችም ሀይል የለም። ስለዚህ በአሁኑ ወቅት በትግራይ ላይ አንዣብቦ የነበረውን የጥፋት ፕሮጀክት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በማስወገድ ህልውናችንና ደህንነታችን በአስተማማኝ አኳኋን ለማረጋገጥና በፅኑ መሰረት ለማኖር ወደምንችልበት ደረጃ ላይ እየተሸጋገርን ነው።

ጀግናው የትግራይ ሰራዊት፣ በትግራይ ህዝብ እሴቶች ላይ የተገነባ ህዝባዊና ጠላቱን ጠንቅቆ የሚገነዘብ ሰራዊት ነው። የሰራዊታችን ህዝባዊነትም ከዚህ ቀደም በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች በተግባር እየተረጋገጠ ነው። የትግራይ ህዝብና መንግስት በራሳቸው ላይ እንዲደርስ የማይፈልጉት ነገር፣ በሌሎች ህዝቦችም ላይ እንዲደርስ ከቶም አይመኙም፣ አይፈቅዱም። ይሁን እንጂ በላያችን ላይ በታወጀው ጀኖሳይድ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የተሳተፉ አካላት ሁሉ፣ ግን ተጠያቂዎች መሆናቸው አያጠያይቅም። በዚህ ጉዳይ ላይ ምንም ምህረት እንደማይኖር መግለፅ እፈልጋለሁ።

በውሸትና በቅጥፈት ሰፊውን ህዝብ በማደናገር ሂደት፣ የአቢይ አሕመደ ፋሽሽት ቡድን የሚያክል ረዥም ርቀት የተጓዘ ያለ አይመስለኝም። ውሸት፣ ቅጥፈትና ማስመሰል ሁነኛ መለያው ያደረገው ይህ ቡድን፣ አሁንም በመቃብር አፋፍ ላይ ቆሞ መዋሽቱን ቀጥሏል። በጊዜ ሂደት ላይ ግን፣ የፋሽሽት ቡድኑ ውሸት፣ ቅጥፈትና ማስመሰል በአለማቀፍ የመገናኛ አውታሮችም ጭምር እየተጋለጠ ነው። በመሆኑም ፋሽሽት ቡድኑ፣ እምነት የማይጣልበት ውሸታም መሆኑን በተግባር እየታየ ነው። የሚገርመው ነገር ግን፣ አሁንም በዚህ አቻ የማይገኝለት ውሸታም የሚደናገሩ መኖራቸው ነው። ለማንኛውም አሁን በውሸትና በቅጥፈት የሚቀየር ነገር የለም። ፋሽሽት ቡድኑ ያሰለፈውን መደበኛ ሰራዊት አስጨርሷል፣ በመሆኑም እንደሌሎች ሁሉ አምባገነኖች ስርአተ ቀብሩ በመጠባበቅ ላይ ነው፣ በቅርቡም ይፈፀማል።

በመጨረሻም የፋሽሽት ቡድን ቅጥረኛ ሰራዊት፣ ለጊዜውም ቢሆን ሶስት ምርጫ አላችሁ። አንድም ለራስችሁ ስትሉ ለሰራዊታችን እጃችሁን በመስጠት ወይም የቡድኑ እኩይ ተልእኮ ጥላቹህ በመሸሽ ህይወታቹህ ማዳን፣ አልያም ደግሞ እጅግ በአጭር ጊዜ ውስጥ እናንተም እንደሌሎቹ ለአንድ ህልመኛ ንግስና ሲባል፣ ህይወታችሁ ማጣት ይሆናል። ከዚህ ውጭ ሌላ ምርጫ የለም፣ ስለዚህ ጊዜውን ተጠቀሙበት ማለት እፈልጋለሁ።

Please wait, video is loading...