Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

መንግሥት ኦባሳንጆ የሚያመጡትን የመፍትሔ ሐሳብ እየጠበቅኩ ነው አለ - ሪፖርተር

Post by sarcasm » 07 Nov 2021, 19:20

ከሰሜኑ ኢትዮጵያ ጦርነት ጋር በተገናኘ የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ ሆነው የተሾሙትና ከሰሞኑ በአውሮፓና ከአሜሪካ አገሮች ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች ጋር ውይይት ሲያደርጉ የነበሩትን የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ፣ ይዘውት የሚመጡትን የመፍትሔ ሐሳብ እየጠበቀ መሆኑን መንግሥት አስታወቀ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና የፍትሕ ሚኒስቴር ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች ተቀማጭነታቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አባላት፣ ሐሙስ ጥቅምት 25 ቀን 2014 ዓ.ም. በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሬድዋን ሁሴን (አምባሳደር) በማብራሪያቸው በፈረንሣይ፣ በቤልጂየምና በኒውዮርክ ጉብኝት እያደረጉ የነበሩትና በቅርቡ ይመጣሉ ብለው የሚጠብቋቸው የአፍሪካ ቀንድ ተዋካይ ምን ዓይነት መፍትሔ ይዘው እንደሚመጡ መንግሥት እየጠበቀ ነው ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት ከዓመት በፊት በሰዓታት ወይም በአንድ ቀን ውይይት ሊፈታ በሚችል አለመግባባበት የተነሳ ሕወሓት በአገር መከላከያ የሰሜን ዕዝ ላይ በፈጸመው ጥቃት፣ መንግሥት ተገዶ ጦርነት ውስጥ እንደገባ ሚኒስትር ዴኤታው አስታውቀዋል፡፡

ሕወሓት በአገር ላይ ጦርነት ከከፈተ በፊትም ሆነ በኋላ ‹‹ወርቃማ›› ዕድሎችን እንዳጠፋ የገለጹት ሚኒስትር ዴኤታው፣ ከጅምሩ በሠለጠነ መንገድ መፈታት ይችል እንደነበር ገልጸው፣ ጦርነት ከገባ በኋላም ቀርቦለት የነበረውን የተኩስ አቁም ስምምነት በመጣሱ ያልተፈለገ ውድመት ስለመድረሱ ለዲፕሎማች አስረድተዋል፡፡

Continue reading https://www.ethiopianreporter.com/article/23683