Page 1 of 1

ህዝብ ከጎኑ ያሰለፈ የመሰለው በተግባር ግን በህዝብ የተፈነፈነው ፋሽስቱ የአብዪ አህመድ ቡድን

Posted: 07 Nov 2021, 18:54
by sarcasm
ህዝብ ከጎኑ ያሰለፈ የመሰለው በተግባር ግን በህዝብ የተፈነፈነው ፋሽስቱ የአብዪ አህመድ ቡድን
*******************************************
በትግራይ ሰራዊት እየተገረፈ በሁሉም ግንባሮች የሽንፈት ውርጅብኝ እየተከናነበ ያለው ይህ በቁሙ የሞተ ወራሪ ቡድን፤ ሽንፈቱን በአንደበቱ መመስከር ተገዷል። ተላላኪ ሚኒስትሮቹን ሰብስቦ በሰጠው ተስፋ መቁረጥ የተሞላበት ማብራሪያ የሚመስል ቁዘማ ላይ "በመደበኛ ሰራዊት ልንመክተው አልቻልንም" ሲል መናገሩ ይታወሳል።

በዓለማቀፉ ማህበረሰብም በዲፕሎማሲ ተፈንፍኗል። መሳሪያ የሚያስታጥቁትና ከጎን አለን ሲሉት የነበሩ እንደ ቱርክና ሩስያ ያሉ ሃገራትም ሳይቀር ወደ ሰላም ድርድር እንዲመጣ እያስገደዱት ይገኛሉ።

የትግራይ ሰራዊት በሁሉም ግንባሮች እያሸነፈ ሰላምን ሲዘምር፤ በአንፃሩ ድል የሰማይ ያህል የራቀው ወራዳ ቡድን የሰላምን በር ዘግቶ ጦርነትን ብቸኛ መፍትሄ አድርጎ ዜጎችን ለተጨማሪ እልቂት ሊማግድ የ "ክተት" ነጋሪት እየጎሰመ ይገኛል። ይባስ ብሎ ሁሉም የመንግስት ሰራተኞችና የሀገሪቱ በጀት ትግራዋይን መልሶ ለመፍጀት እንዲውል ቀጭን ትእዛዝ አስተላልፏል።

ይህ በህዝብ ይሁንታ የተነፈገና የተፈነፈነ ፋሽስት ቡድን የሀገሪቱን ህዝብ ከጎኑ ለማሰለፍ የመጨረሻ ያለውን ዕድል በተለያዩ ከተሞች ሰልፍ በማካሄድ ሞክሯል። ውጤቱ ግን በተገላቢጦሽ በው የሆነበት።

በአዳማ በተካሄደው ሰልፍ፤ በአምባገነኑ አብዪ የታሰሩ የኦሮሞ ፖለቲከኞች እንዲፈቱ በመጠየቃችው ምክንያት ሰልፉ ሊበተን ግድ ሆኗል። ዛሬ በአዲስአበባ በተካሄደው የድጋፍ የተባለው ሰልፍ ላይም ተመሳሳይ ፍፃሜ ነው የተስተዋለው። ከደቡብ የመጣው ታሪኩ ጋንካሲ የተባለው ድምፃዊ ከሰልፉ መድረክ ሙዚቃ እንዲያቀርብ ሲታደም "ሙዚቃ ሲደላ ነው" ብሎ እንደ ስሙ ታሪካዊ ንግግሩን ጀመረ። አስከትሎም ሰላም ጠፋ! ወጣቶችን ሳይሆን ሽማግሌዎችን እንላክ! ይብቃ! ይብቃ! ሲል የፋሽስቱን አብዪ ሴራ በነገር ሸንቆጥ አደረገው።

እነዚህ ተግባሮች ሁሉ ፋሽስቱ የአብዪ አህመድ ቡድን የኢትዮጵያን ህዝብ ከጎኑ ያሰለፈ የመሰለው በተግባር ግን በህዝብ የተፈነፈነ ስለመሆኑ ማረጋገጫዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ህዝብ አብዪ ለስ ጣኑ ሲስገበገብ እንጂ ለዜጎች ደህንነት ቅንጣትም ታክል ደንታ እንደሌለው ዘግይቶም ቢሆን ተገንዝቦታል። የአብዪና ግብረአበሮቹ መቀመቅ የሚወርዱበት ጊዜ እጅጉን አጭር ነው የምንለውም በምክንያት ነው።

ትግራይ ትስዕር!
Please wait, video is loading...