Page 1 of 1

<<<{{{BREAKING NEWS}}}>>>ድብቅ መረጃ:ከዲፕሎማቶች ኮሪደር የተገኘ!!! WEEY GUUD !!!

Posted: 07 Nov 2021, 12:55
by tarik
Natnael Mekonnen
454ftcpf7t113lleh8 ·
ድብቅ መረጃ! ከዲፕሎማቶች ኮሪደር የተገኘ።
#Ethiopia : ኢትዮጵያን ለማፍረስ ከሕወሓት ጋር የገጠሙት ምዕራባውያን በሰሞኑ የሕዝብ እንቅስቃሴ ተበሳጭተዋል። በሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝብ ለመዝመት መነሣቱና ከሰሞኑ ሕዝቡ በየአቅጣጫው የታየው ትዕይንተ ሕዝብ ምዕራባውያኑ ሌላ አማራጭ እንዲያዩ አድርጓቸዋል።
ከሰሞኑ ከዲፕሎማቲክ ኮሪደር የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው አያሌ ኤምባሲዎች፣ የውጭ ሲቪክ ተቋማትና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ሠራተኞችን ወደ ኢትዮጵያ በገፍ ለማስገባት ጠይቀዋል። በአንድ በኩል በሀገር ውስጥ ያሉትን ሠራተኞቻቸውን ውጡ ይላሉ። በሌላ በኩል ሠራተኞችን ከውጭ ለማስገባት ይጠይቃሉ። ከአንዳንድ ዲፕሎማቶች እንደተሰማው እነዚህ ኤምባሲዎች፣ የውጭ ሲቪክ ተቋማትና ዓለም አቀፍ ተቋማት ወደ ኢትዮጵያ በገፍ ሠራተኞችን ለማስገባት የጠየቁት የሠለጠኑ ነፍሰ ገዳዮችን ወደ ኢትዮጵያ ለማምጣት ነው። የሠለጠኑ ነፍሰ ገዳዮችን የሚያሠለጥኑ ተቋማትን አንዳንድ ዲፕሎማቲክ ድርጅቶች አናግረዋቸዋል።
እነዚህ ነፍሰ ገዳዮች ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጡ የተፈለገው ጠቅላይ ሚኒስትሩንና በዙሪያቸው ያሉትን ታዋቂ ሰዎች ለማጥፋት መሆኑ ታውቋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ የኤምባሲና የኤን.ጂ.ኦ. ሰዎችን ጉዳይ በጥንቃቄ ማየት እንዳለባቸው ውስጥ ዐዋቂዎች ተናግረዋል። ሕዝቡም በየአካባቢው የሚደረገውን እንቅስቃሴ በንቃት እንዲከታተል ተመክሯል።