Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4487
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

ኦነግ የትግሬ ወራሪ ኦሮሚያ ዉስጥ አይግባብኝ ሲል መግለጫ አውጥቱኣል። ለአማራ ና አፋር የተደገሰውን ሊቋደሱት ነው፥)

Post by Za-Ilmaknun » 04 Nov 2021, 18:11

ትርጉም አልባ ወደ ሆነ ጦርነት ህዝቦች ተገፋፍተው እንዲሳተፉ በሚደረገው ጥሪ ላይ ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር(ኦነግ) የተሰጠ መግለጫ :mrgreen: :mrgreen:

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) መግለጫ - ጥቅምት 24/2014

የኢትዮጵያ ህዝቦች በተለይም የኦሮሞ ህዝብ ለአንድ ክፍለ ዘመን በላይ በማይመለከታቸው እና ባልተገባ ጦርነት ያለማቋረጥ መማቀቃቸው እጅግ አሳዛኝ ነው። የኢትዮጵያ ኢምፓየር ከተመሰረተ ጀምሮ ከእርስ በርስ ጦርነት ነጻ ሆና የኖረበት ጊዜ የለም። አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ የዚህ የማያባራ ጥልፍልፍ ጦርነት ሰለባ እንደሆነ ቀጥሏል። በተለይ ደግሞ ሰላም ወዳዱ የኦሮሞ ህዝብ ምንም እንኳን ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ የመፍታት የዳበረ ባህል ያለው ቢሆንም በገዥዎች ስርዓት ፍላጎት በሚከሰተው ግጭት እና ጦርነት ሰለባ ሆኖ እንደቀጠለ ይገኛል። አብዛኛውን ጊዜ በጉልበትና በጦርነት የስልጣን ኮርቻውን የሚቆጣጠሩት ራስ ወዳድ አምባገነን የኢትዮጵያ ነገስታቶች የኦሮሚያን ዜጎች እና ሌሎች የሀገሪቱን ዜጎች ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍ ጦርነት ውስጥ ጥለው ማለፍ የተለመደ ነው። ይህ አምባገነንነት የተጠናወተው ፈላጭ ቆራጭ ስርዓት ሀገሪቱን ለማያባራ ግጭት እና ጦርነት ከመዳረጉ በተጨማሪ ተጨባጭ የሆነ እድገት እና የዜጎች ህይወት ላይ ለውጥ እንዳይታይ የጎላ ጠባሳ ጥሏል።

የኦሮሞ ህዝብ ይህንን በግጭት እና ጦርነት ላይ የተመሰረተውን ስርዓት ለአንድ ክፍለ ዘመን በጽኑ ሲታገል እና ሲቋቋም ቆይቷል። በተለይም ኦነግ ከተመሰረተበት ከ50 አመት ወዲህ የራስን እድል በራስ የመወሰን ብሔራዊ ትግል ከተጀመረበት ግዜ ጀምሮ ይህንን በግጭት ላይ የተመሰረተ አምባገነናዊ ስርዓት ለማስወገድ ከፍተኛ መሰዋዕትነት ተከፍሏል። ይህንን አምባገነናዊ ስርዓት ቀይሮ ዲሞክራሲያዊ ስርዓትን የማስፈን የትግል ሂደት ውስጥ የኦሮሚያ ዜጎች በተለይ ደግሞ አያሌ የኦሮሞ ወጣቶች እጅግ ከፍተኛ ዋጋ ከፍለዋል።

ይሁን እንጅ ተከታታይ የኢትዮጵያ ስርዓቶች በተለይም ደግሞ የብልጽግና ፓርቲ ከሰላም ይልቅ የጦርነት አማራጭን በመምረጥ ግጭቶችን በመደራረብ የኢትዮጵያን ህዝቦች ወደማያባራ ጦርነት ወስጥ በማስገባት በሀገሪቱ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ዘግናኝ አልቂቶች እየታዩ ይገኛል። ኦነግ እየተደረገ ያለውን ተደጋጋሚ የጦርነት ነጋሪት ጉሰማና ጥሪ በእጅጉ ያወግዛል። ሰሞኑን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት (የብልጽግና ፓርቲ ኦሮሚያ ክንፍ) ጦርነቱን ለማፋፋም እና ተቃራኒ ተፋላሚ ወገኖችን ለማስወገድ ያደረገውን የክተት ጥሪ በእጅጉ እናወግዛለን። ይህ "መዋጋት የሚችል ሁሉ" በሚል በመጨረሻ ሰዓት ለይ የሚደረግ የክተት ጥሪ የዜጎችን ህይወት በመገበር የብልጽግና ፓርቲ ባለስልጣናትን እድሜ ለማራዘም ካልሆነ በስተቀር ለሀገሪቱ ሰላምም ሆነ መረጋጋት አንዳች ፋይዳ የለውም። ንጹሃን ወጣቶችን እና አምራች ዜጋን ባልተገባ ጦርነት ለመማገድ የሚደረገው ጥሪ በትውልድ ላይ ወንጀልን መስራት በመሆኑ ኦነግ በጥብቅ ይቃወማል ፣ያወግዛል። ይሆ የክተት ጥሪ ትውልድን ከማጥፋት እና ንጹሀን ዜጎችን ህይወት ከመቅጠፍ ባለፈ የሀገሪቱን ሀብት አውዳሚ በመሆኑ እጅጉን እናወግዛለን።

የኦሮሚያ ዜጎች በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የተደረገውን የክተት ጦርነት ጥሪ ውድቅ በማድረግ በተቃራኒው የራሳቸውን ክልላዊ አስተዳደር በምቆጣጠር እና ድንበር ኸሚሊሻ ወራሪዎች እንዲከላከሉ እና እንዲጠብቁ በጥብቅ እናሳስባለን። የኦሮሚያ ዜጎች የራሳቸውን የአስተዳደር መዋቅር እንዲያጠናክሩ ፣ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ የሽግግር መንግስትን በማረጋገጥ ላይ እንዲሰሩ እና ራሳቸውን እንዲጠብቁ ኦነግ ጥሪ ያስተላልፋል። እያንዳንዱ የኦሮሚያ ዜጋ በጥብቅ ማወቅ ያለበት ብልጽግና ፓርቲ ሆን ብሎ በማቀድ ኦሮሚያን ለማተራመስ እየሰራ መሆኑን ነው። ይህንን ሴራ በንቃት መከታተል እና አክሽፎ የኦሮሚያን እና የዜጎቿን ሰላም ማረጋገጥ ጊዜው የሚፈልግባችሁ ጥብቅ ሀላፊነት ነው። በተጨማሪም የኦሮሚያ ዜጎች ከጎረቤት ክልሎች እና ህዝቦች ጋር ያላቸውን ሰላም እና አብሮነት እንዲያጠብቁ ጥሪ እናስተላልፋለን።

በዚሁ አጋጣሚ ህወሀት(TPLF) እና ሀይላቸው ትመሀ(TDF) የኦሮሞ ህዝብን ሉዋላዊነት እንዲያከብሩ እና የጦር ሀይላቸውን ወደ ኦሮሚያ ድንበር ውስጥ ከማስገባት እንዲቆጠቡ ለማሳሰብ እንወዳለን። የማሳሰብያ ምክንያታችንንም እንደሚረዱ ተስፋ እናደርጋለን።

የኢትዮጵያ ዜጎች ገጭትን የሚያባብሱ የትኛውንም ጥሪዎችን ውድቅ እንዲያደርጉ እና በተቃራኒው ሰላማዊ የሆነ ሁሉንም ያሳተፈ ህብረ ብሔር የሆነ የፈደራል ስርዓት መልስዉ እንዲቋቋሙና እንዲጥሩ፣ ሰላም እና መረጋጋት እንዲሰፍን በአብሮነት እንዲሰሩ እና ነጻ እና ተአማኒ የሆነ ምርጫ በማካሄድ የፖለቲካ ዉይይት እውን ለማድረግ የበኩላችሁን አስተዋጽኦ እንድታደርጉ ኦነግ ይመክራል።

የአለም አቀፍ ማህበረሰብ ሀገሪቱ ካለችበት ዘርፈ ብዙ ችግሮች እንድት ወጣ ግጭቱን በሚያባብሱት አካላት ላይ ጫና መፈጠር፣ አሳታፊና የሆነ ዘላቂ መፍትሄ በመፈለግ እና መተግበር ላይ የራሳቸውን ሚና እንዲጫወቱ ብሎም ሰላማዊ የፖለትካ ምክክር እና የሽግግር ህደት እንዲፈጠር ያላሳለሰ ጥረት እንዲያደርጉ ኦነግ ያሳስባል።

ድል ለሰፊው ህዝብ!

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር/ኦነግ/

ጥቅምት 24/2014

ፊንፊኔ

Sam Ebalalehu
Member
Posts: 3639
Joined: 23 Jun 2018, 21:29

Re: ኦነግ የትግሬ ወራሪ ኦሮሚያ ዉስጥ አይግባብኝ ሲል መግለጫ አውጥቱኣል። ለአማራ ና አፋር የተደገሰውን ሊቋደሱት ነው፥)

Post by Sam Ebalalehu » 04 Nov 2021, 18:38

Za, this is a TPLF letter. I understand their Amharic. The Oromos most likely do not use the Amharic “metelalef.” It is a TPLF cadre word, trying to be impressive. They might have copied from Meles, who used to love using some words that enlightened Addis residents use to make himself a well-rounded person. Another TPLF word is “hageritu.” They really hate to say Ethiopia. I can pick many vocabularies from the letter, but you get the idea.

Post Reply