Page 1 of 1

አስደሳች ዜና

Posted: 04 Nov 2021, 14:51
by Educator
አስደሳች ዜና፡-
እውነትን ለምትወዱ ለፍትሃዊ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ!!

እነሆ ዛሬ እረጅም ግዜ የፈጀው የአቃቤ መንግስት የሃሠት ምስክር የሆነው የአሠልቺው የስድስተኛው የወርቁ ታደሠ ቶላ የምስክር መሠማት ሂደት የተጠናቀቀ ሲሆን ከመጀመሪያው ከባድ ወንጀለኛ የሃሠት ምስክር አቶ ይባስ አሠፋ ደበሌ ጀምሮ እስከ ዛሬው ስድስተኛ ምስክር ወርቁ ታደሠ ቶላ ድረስ አንድም ምስክር በአቃቤ መንግስት ተደርሶ የተሠጠውን የሃሠት እስክሪብት አጥንቶ በእነ እስክንድር ላይ ሊመሠክር በፍፁም አልቻለም በተለይም አቃቤ መንግስት ያቀረባቸው የሃሠት ምስክሮች እጅግ አደገኛ ወንጀለኛ እና አብዛኞቹም ከዚህ በፊት በሃሠት የመመስከር ልምድና ብቃቱ ያላቸው ቢሆንም እነሡን በውሸት ያሠለጠናቸውና ያስጠናቸው አካል
(አቃቤ መንግስት) የሃሠት እስክሪብቱን ሲፅፍ ብዙ ነገሮችን በማጉደሉና የፃፈውንም የውሸት ድሪቶ በደንብ ማስጠናት ባለመቻሉ እንዲሁም ሸምድደው የአጠኑትንም የውሸት መአት ለእውነትና ለሃቅ የቆሙት ጀግኖቹ ጠበቆቻችን ሄኖክ አክሊሉ ቤተማሪያም አለማየሁ እና ሠለሞን በመስቀለኛ ጥያቄ እያፋጠጡ እርቃናቸውን ስላስቀሩአቸው ተዋርደውና ተሸማቀው ከችሎት አንገታቸውን እየደፉ አቀርቅረው ሊወጡ ተገደዋል።
በዚህም ምክንያት እጅግ የተደናገጡት አቃቤ መንግስቶች በዳኛ ትዕዛዝ ሌሎቹን ምስክር አቅርቡ ቢባሉም ሠባተኛው ምስክር ኮረና ይዞት ማገገሚያ ገብቱአል ሌሎቹ ሶስቱ ምስክሮቻችን ደግሞ ሊቀርቡልን ፍቃደኛ ስላልሆኑ ፍ/ቤቱ በግድ መተው እንዲመሠክሩ መጥሪያ ይፃፍልን ብለው ግዜ ለመውሠድ የማይረባና አሳማኝ ያልሆነ ምክንያት አቅርበዋል።
ከአቃቤ መንግስት ጥያቄ በኃላ ጀግኖች ጠበቆቻችን ለችሎቱ አቃቤ መንግስት ምስክር ማቅረብ ስላልፈለገ እና ስላልቻለ ፍ/ቤቱ የምስክር ሂደቱን እዚህ ላይ አቁሞ እስከዛሬ በተሠማው ላይ ውሳኔ ይስጥልን ብለው ተገቢ ጥያቄአቸውን ያቀረቡ ሲሆን ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር አዳምጦ
ምስክር ይቀጥል ይቁአረጥ ለሚለው ውሳኔ ለመስጠት ለነገ ቀጠሮ ይዙአል።

እውነትን የያዘ ምንግዜም ያሸንፋል!
እናት ኢትዮጵያም በሁሉም ቦታ ታሸንፋለች!

#አሌክስ ሸገር
ከኢትዮጵያ ዋና ከተማ
#አዲስ አበባ