Page 1 of 1

The damning UN Human Right report accuses TPLF fascists for atrocities they committed in Mai-kadra and elsewhere

Posted: 03 Nov 2021, 11:51
by Za-Ilmaknun
We all have come to the conclusion long ago that the UN and US are not interested in the facts regarding the raging war ignited a year ago by TPLF fascism. However, for the rest of us the report is one more evidence that proves the barbarism of the Tigre invaders and the indifference of the West for real violations if it doesn't promote their agenda.

TPLF fascism is enemy to humanity and, it has to be stopped once and for all. :|


Re: The damning UN Human Right report accuses TPLF fascists for atrocities they committed in Mai-kadra and elsewhere

Posted: 03 Nov 2021, 18:08
by Za-Ilmaknun
ምዕራባዊ ሚዲያዎችን ያስደነገጠ የራሳቸው ተቋም ሪፖርት
እስሌማን ዓባይ

አለማቀፍ የርዳታ ተቋማትና ሠራተኞች፣ አሜሪካና አውሮፓ ህብረት፣ ዲፕሎማቶናና የምዕራባዊያን ሚዲያዎች የኢትዮጵያ መከላከያ በትግራይ ክልል የሰብአዊ መብት ጥሷል የጦር ወንጀልም ፈፅሟል በማለት ተደጋጋሚ የክስ ውርጅብኛና ጩኸት ሲያሰሙ ነበር። ክሶቹ የህወሃት አመራሮችን እና አክቲቪስቶችን ቃል ዋቢ በማድረግ ነበር። ከጊዜ በኋላ ደግሞ አለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን እና የኢትዮጰያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን የጋራ ምርመራ ማድረግ ጀመረዋል። ከመስከረም 05 ቀን፣ 2014 ዓ.ም. ጀምሮ በተደረገው ምርመራ የተደረሰባቸው ግኝቶች ከትላንት በስቲያ ሌሊት በኒውዮርክ በተደረገ መግለጫ ይፋ ተደርጓል።

በመግለጫው ይፋ የሚሆኑ የመብት ጥሰት ግኝቶችን ለመዘገብ ለህወሃት በመቆም የሚታወቁ ሚዲያዎች ጓጉተው ነበር። እነ ቢቢሲ፣ አዲስ ስታንዳርድ መግለጫ ሊሰጥ ስለመሆኑ ዛቻ መሰል ቅድመ ጥቆማ ሲሰጡ ነበር። በተለይም የጀርመኑ DW አማርኛ ድርጊት ብዙ የሚያስብል ነበር። ሌሊት የሚሰጠውን መግለጫ በፌስቡክ ገፁ በቀጥታ እንደሚያሰራጭ ቀን ላይ አስቀድሞ አስታውቆ ነበር። መግለጫው ከተሰጠ በኋላ ግን ነገሮች ተለወጡ። የምርመራ ግኝቶቹ የህወሃትን ወንጀሎች በስፋት አስቀመጡ። የሪፖርቱን ዘገባ መስራት አልፈቀዱም። አዲስ ስታንዳርድ፣ ቢቢሲ አማርኛ፣ DW አማርኛ ወዘተ እና መሰሎቻቸው ዝምታን መረጡ።
በምርመራው ሪፖርት ከተገለፁ ግኝቶች መካከል፦

መንግስት የዘር ማጥፋት ወንጀል አልፈጸመም። ለክሱም ማስረጃ እንዳልተገኘ፤ መንግስት የትግራይን ሕዝብ በሰው ሰራሽ በሆነ ድርጊት ሆን ብሎ አለማስራቡ፤ ጾታዊ ጥቃትን እንደ ጦርነት መሳሪያ ስለመዋሉ መረጃ እንዳልተገኘ፤ ሳምሪ የተባለው የህወሃት ገዳይ ቡድን ከህወሃት አመራሮች በመቀናጀት 200 የአማራ ተወላጆች ማይካድራ ላይ እንዲጨፍጨፉ መሆናቸው መረጋገጡን፤ ሕወሓት የኢፌድሪ መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት መሰንዘሩ ለዚህ ሁሉ ቀውስ መነሻ መሆኑ በኒውዮርክ የኮሚሽኑ አዳራሽ ይፋ ተደረገ።

የሕወሓት አጋር ሆነው የተጓዙት የምዕራባዊያን አገራት መንግሥታትና ተቋማት እንዲሁም ብዙኃን መገናኛዎች ከራሱ ከወንጀለኛው ሕወሓት አመራሮች ብቻ በወሰዱት ሀሰተኛ መረጃ ተመስርተው የመንግሥት ኃይሎች የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈፅሟል ሲሉ የከረሙት ውድቅ ይሆናል ብለው እንዳላሰቡ መረዳት አይከብድም። ለዚህ ማሳያ የሚሆነን ከኒውዮርኩ ሪፖርት በፊት ኢትዮጵያ ውስጥ የተሰጠውን የምርመራ ሪፖርት ዘና ብለው መዘገባቸው ነው።

ምዕራባዊ ሚዲያዎቹም ሆኑ እነ አዲስ ስታንዳርድ "በአማራና አፋር የሕወሓት ታጣቂዎች እጅግ አሰቃቂ ወንጀሎችን በኅብረተሰቡ ላይ ስለማድረሳቸው የፍትህ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ዘርፍና ፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጽ/ቤት በጋራ ለሰጡት መግለጫ ሽፋን ሰጥተው ነበር።
በዚህም የሕወሓት ታጣቂዎች ይዘዋቸው በነበሩና «ኋላ ላይ በሕግ ማስከበሩ ዘመቻው ነጻ በወጡ አካባቢዎች ላይ» ከአሰቃቂ የአስገድዶ መድፈር፤ እስከ ነፍስ ማጥፋት ወንጀሎች መፈጸማቸው ተገልጧል" ብለው ለመዘገብ አልተቸገሩም ነበር። በተለይም DW አማርኛ "በተጠቀሱት አካባቢዎች 482 ሰዎች በሕወሓት ታጣቂዎች መገደላቸውን፣165 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱን፣ 109 የአስገድዶ መድፈር ተግባር መፈፀሙን፣ የ6 ወር ህጻን የእናቱን ጡት እንደያዘ በከባድ መሣሪያ ከእነ እናቱ ተመትቶ መገደሉ፤ በቤተሰቦቻቸው ፊት በተናጠልም በደቦ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ከተፈጸመባቸው ሴቶች መካከል የ7 ወር ነፍሰ ጡር ሴት በሦስት የህወሃት ሃይሎች መድፈሯ" እንደሚትገኝበትም ይፋ የሆነውን መግለጫ ጠቅሶ ዘገበ።

የጋራ ምርመራ ሪፖርቱ በተ.መ.ድ የሰብኣዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር በኩል የቀረበው ሪፖርት እነ DW እንዳሰቡት ተገልብጦ ባለመቅረቡና ራሱ መሆኑን ሲመለከቱ በዝምታ ተዋጡ። ዛሬ ላይ የእነ ቢቢሲ DW አማርኛ እና አዲስ ስታንዳርድ ገፆችን በረበርኩ። ወደ ኋላ ተመልሼ ብፈትሽም ስለ ኒዮርኩ ሪፖርት አንድም ዘገባ አልሰሩበትም። በጣም የሚገርም ነው። ጉዳያቸው ሰብአዊ መብት አለመሆኑ ይበልጥ ገሃድ ወጣ ማለት ነው። እስከዛሬ ያልተገለጹ የህወሃት ኃይሎች በርካታ ወንጀሎችም መኖራቸውን ለሩቁም ለቅርቡም የሚጠቁም እና በአንፃሩ ኢትዮጵያዊያን ሲያሰሟቸው የነበሩ ድምፆችና መረጃዎችን ተዓማኒነት የሚያሳድጉ ናቸው ማለት ይቻላል።

CNN እንደምንም ብሎ ጉዳዩን ለመዘገብ ሞክሯል። ዘገባውን ለማቅረብ ሪፖርቱ ይፋ ከሆነ በኋላ ከ24 ሰዓት በላይ ዘግይቶ ነበር Nov3 ላይ ለህወሃት ያለውን ውግንና በሚያሳብቅ አቀራረብ ዜናውን ያቀረበው። የኒዮርኩ የምርመራ ሪፖርት የዘረዘራቸውን የህወሃት ወንጀሎች ከመጥቀስ ይልቅ በደምሳሳው ወንጀል መፈፀሙን ብቻ ነው የጠቀሰው። ከዚህ ይልቅ "ወንጀሎች በመከላከያም በህወሃትም ሳይፈፀሙ አልቀሩም" የሚለውን መላምት ነው ለማጉላት የሞከረው። ልብ በሉ፣ ይህ ግምት መላምታዊ እንጂ የምርመራው ውጤት ውስጥ አልተቀመጠም። የምርመራ ሪፖርቱን ባቀረቡበት ወቅት የዘረዘሩት የህወሃትን ወንጀሎች ብቻ ነው። በተረፈ ቀጣይ ምርመራ ቢደረግ በመከላከያም ሆነ በኤርትራ ሰራዊት ጥሰት ተፈፅሞ ሊሆን ይችላል ነው የተባለው። በመላምት ብቻ..። CNN ከግኝቱ ይልቅ መላምቱን ለማጉላት እንዴት ተጨንቆ እንደዘገበው መታዘብ ይቻላል።
በሪፖርቱ የህወሃት ሰዎችም እጅጉን ተበሳጭተው ነበር። ጌታቸው ረዳ፣ ዲጂታል ወያኔዎችና አንዳንድ አመራሮቻቸው አለማቀፉ ምርመራ አድሏዊ ነው ሲሉ አማርረዋል። እኛን በደምብ አላሳተፉም ሲሉም ወቅሰዋል። እነዚያ ተቋማትኮ የህወሃት አጋሮች የነበሩ ናቸው። ባይሆኑ ኖሮ የበለጠ ወንጀል ባስቀመጡና የህወሃትን ሽብር ለዳኝነት በጋበዙ ነበር። ሪፖርቱ ውድቅ ካደረገው የትህነግ ክስ ውስጥ "የአክሱም ጭፍጨፋ" የተባለው ይገኝበታል። ምንም ማስረጃ የለም ነበር የተባለው። ፈጣሪ ያሳያችሁ፤ አክሱም ላይ ጭፍጨፋ መደረጉንኮ አለማቀፍ ተቋም ተብየው አምነስቲ february25 ላይ ነበር ይፋ ያደረገው። በማግስቱ ደግሞ axum massacre በሚል ለሽታግ ዲጂታል ወያኔ የትዊተር ዘመቻ ጀመረ። ይህ ሁሉ ውሸት ውሃ በላው ማለት ነው። አምነስቲም እንደ ህወሃትና አጋር የምዕራብ ሚዲያዎች እንዲህ ተጋለጠ። የተጋለጠው ደግሞ በራሳቸው ተቋም በኩል መሆኑ ነው።
በዚህ ውስጥ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በምርመራው በጋራ በመሳተፍ የሰራው ተግባር ታላቅ ነበር ማለት ነው። ዜጎች በዲጂታል ዘመቻው ያሰማነው ጩኸት እንዲሁም የርዳታ ጫኝ መኪኖችና አፍቃረ ህወሃት የተመድ ሰራተኞችን ወንጀል በተከታታይ ያንፀባረቅንበት ዘመቻ እንዲሁም እነ ጄፍ ፒርስ አን ጋሪሰን ማውሪን እና....ያሉ ስለ እውነት የደከሙ የውጭ ዜጎች አበርክቶ የጀግና ተግባር ቢባል ያንሳልንጂ አይበዛበትም።

አለማቀፉ የመብት ኮሚሽን ቀጣይ ምርመራና ሪፖርት እንደሚኖር ጥቆማ የሰጡበት ሲሆን፣ ይኸውም ህወሃትና አጋር ምዕራባዊ አጋሮች በሂደት እንዳይጠመዘዝ ዘመቻችን ቀጣይነት እንደሚያስፈልገው አመላካች ነው።

ውሸትና ስንቅ እያደር ያልቅ

ኢትዮጵያ ለህወሃት ቀብር እንጂ ወንበር የላትም
እናሸንፋለን
እስሌማን ዓባይ-የዓባይ ልጅ

Yonatan TR
Iyoba ForGerd
Birhanu M Lenjiso
Shumet Gizaw
Jeff Pearce
Dejene Assefa
Francesca Ronchin