ሰበር ዜና፡ የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት በህልውና ዘመቻው ለመሳተፍ ትምህርት እንዲቋረጥ ጠየቀ
Posted: 02 Nov 2021, 09:57
የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት በህልውና ዘመቻው ለመሳተፍ ትምህርት እንዲቋረጥ ጠየቀ
********************
የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት በህልውና ዘመቻው ለመሳተፍ ትምህርት እንዲቋረጥ ጠይቋል፡፡
የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ህብረት ከተማሪዎች ጋር ባደረገው ውይይት ተማሪዎቹ ትምህርት ተቋርጦ ለህልውና ዘመቻው በተለያየ መልኩ ድጋፍ ለማድረግ መወሰናቸው ተገልጿል።
የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ህብረት ፕሬዝዳንት ተማሪ ብርሃኑ ታደሠ ተማሪዎቹ ወረራው ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በገንዘብ፣ ደም በመለገስና የህብረተሠቡ ድምፅ በመሆን ሲደግፉ መቆየታቸውን ገልጿል።
አሸባሪው ትህነግ በሀገር ላይ የደቀነው የህልውና ስጋት በመደበኛ የህግ ማስከበር ሂደት የሚፈታ ባለመሆኑ የክልሉ መንግስት ባወጀው መሠረት ተማሪዎች ግንባር ቀደም በመሆን ዘመቻውን ለመቀላቀል መወሰኑን ህብረቱ አስታውቋል።
ትምህርት የአካል፣ የአእምሮና የስነልቦና ዝግጅት የሚጠይቅ ነው፤ ሀገር በሰላም እጦት ውስጥ ሆና ተረጋግተን መማር አልቻልንም ብሏል፡፡
አሸባሪው ህወሓት በዜጎች ላይ እያደረሰው ያለው በደል ተማሪዎቹን ቁጭት ውስጥ የከተታቸው በመሆኑ ግንባር ከሚገኙ ወንድሞቻቸው ጋር በመሰለፍ ለመፋለም መወሰናቸውን ህብረቱ ገልጿል።
ኢትዮጵያውያን በታሪክ አሸናፊዎች የሆኑት ሁሉንም ልዩነቶች ወደጎን አድርገው ለአንድ ዓላማ በመቆማቸው መሆኑን የጠቀሱት ተማሪዎቹ ዩኒቨርሲቲው ጥያቄአቸውን እንዲቀበላቸውና መንግስትም ወታደራዊ ስልጠናዎችን እንዲያመቻችላቸው ጠይቀዋል።
በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በመደበኛው መርሃ ግብር ብቻ ከ16 ሺህ በላይ ተማሪዎች በ7 ካምፓሶች ትምህርታቸውን እየተከታተሉ እንደሚገኙ ታውቋል፡፡
ጠቃሚ የጤና መረጃ
የልብ ድካም መንስኤዎችና መከላከያ ወሳኝ መንገዶች። ለጥንቃቄ መታየት ያለበት። መፍትሄዉ በእጃችን ነዉ:: ለማየት ሊንኩን ወይም ምስሉን ይጫኑ