Page 1 of 1

'ቲቲቪ ፎረም' - ጀነራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ ያነሷቸዉ አንኳር ነጥቦች Finfinne Times Summary

Posted: 02 Nov 2021, 09:06
by sarcasm
ከዛሬው ቃለመጠይቅ ...

*️ ከጠ/ሚ/ሩ ጋር በግሌ 3ት ጊዜ አግኝቼ-ከትግራይ ህዝብ ጋር እየተጣላ መሆኑ:ይህም በሰላም እንዲፈታው በዚህም እንደማግዘው ነግሬዋለሁ:: ከደመቀ ና ብርሀኑ ጁላ ጋርም እንዲሁ::

*️የትግራይ ህዝብ ለዚህች ሀገር ብዙ መስዋዕት ከፍሏል (በኔ ዕድሜ እንኳን የማስታውሰው) ነገር ግን አመድ አፋሽ ነው የሆነው:: ዲያቆኑ:ጳጳሱ በለው ነው እያሉ ያሉት (በጣም ከጥቂቶች በስተቀር)

*️የትግራይ ህዝብ ቆም ብሎ: አስቦ የራሱን ውሳኔ መወሰን አለበት

*ለዚህ ታሪክ መብቃቴ ኩራት ይሰማኛል:ወደን ፈልገን ያመጣነው አይደለም ከልጅ: ልጅ-ልጆቻችን ጋር መሆን ነበር የምንፈልገው: የተሻለ ኑሮም ነበረን
* ለትግራይ ህዝብ ይህን ማድረጌ እንደ እድለኝነት ነው የምቆጥረው .. ይህንን የማያደርግ ደግሞ ፈሪ ነው
* ️ጀግና ሰውን ያከብራል: ጀግና ሴት አይደፍርም: ጀግና አይሰርቅም: ጀግና ንብረት አያወድምም: ጀግና ትሁት ነው ይሄን ሁላ የሚያደርግ ፈሪ ነው
* ️የኤርትራ መንግስት ለጦርነት ዝግጅት ማድረግ አይጠበቅበትም ምክንያቱም ኤርትራ ውስጥ 12 ክፍል ጨርሰህ ወደ ጦር ካምፕ ትገባለህ ከዛ ኢሳያስ ወደ ሚያሰማራህ ትሄዳለህ
* ኢሳያስ ኢ/ያ ውስጥ እንደፈለግኩ ልሁን ሲል "ተው" ስለተባለ ብቻ ፖሊሲ ቀርፆ ሀገሩ መለወጥ ሲችል ለሁሉም ነገር ውድቀቱ #ወያኔ እያለ ጥላቻ ና ቂም ነበረው
* አሁን የሚፈልገው አግኝቷል በተቻለው አቅም ትግራይን አውድሟል:ኢ/ያ ውስጥ ያሉትም ከ27 በላይ በመንግስት የሚታወቁ የምንዛሬ ቢሮዎች ተቆጣጥሯል
* ወደ ኤርትራ ሚሳይል ከመተኮሱ በፊት ዛላንበሳ ላይ ከ2ት ሳምንት በላይ ከኤርትራ ጋር ተዋግተናል
* ህወሓት ታንኩም ባንኩም ትቶላቸው ወደ ክልሉ መጥቶ ህዝቤ ላስተዳድር ሲል: "አታስተዳድርም ከፈጣሪ ቀጥሎ ኢ/ያ ውስጥ ያለው የአማራው ሀይል በሚለው ነው መሄድ ያለብህ ነው ያሉት"
* የአማራ ህዝብ እንደሌላው ህዝብ ሰርቶ መኖር እንጂ የበላይነት ኑሮት (ኤሊቶቹ እንደሚሉት) ለመኖር አይደለም የሚፈልገው
* ️የኢ/ያ ችግር ብቻችን እንፈታዋለን ብለን አናቅም : የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች እና ፖለቲከኞች የተካተቱበት የሽግግር መንግስት ይፈልጋል
* ️በታሪክ የራሱን ህዝብ ከውጭ ሁኖ የወረረ መሪ እኔ አላውቅም
* ምኒሊክ ለጀመረው ስርዓተ መንግስት ለመቀጠል ስጋት ይሆንብናል ብለው ያሰቡት ህወሓት ና የትግራይ ህዝብ ነው



Please wait, video is loading...

Re: 'ቲቲቪ ፎረም' - ጀነራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ ያነሷቸዉ አንኳር ነጥቦች Finfinne Times Summary

Posted: 03 Nov 2021, 04:05
by Meleket
sarcasm wrote:
02 Nov 2021, 09:06
ከዛሬው ቃለመጠይቅ ... . . .
* ️ጀግና ሰውን ያከብራል: ጀግና ሴት አይደፍርም: ጀግና አይሰርቅም: ጀግና ንብረት አያወድምም: ጀግና ትሁት ነው ይሄን ሁላ የሚያደርግ ፈሪ ነው
.
* ወደ ኤርትራ ሚሳይል ከመተኮሱ በፊት ዛላንበሳ ላይ ከ2ት ሳምንት በላይ ከኤርትራ ጋር ተዋግተናል

“ወሓጥዮ እንተበልኵዋስ ትጎስሞ” :mrgreen:

ወዳጄ ታድያ ጀግና፡ አድያቦና ዛላምበሳ ላይ ፊትለፊት የገጠመህን ሰራዊት ትገጥማለህ ሚሳይልህንም በጦር ሜዳ ላይ ትተኩሳለህ እንጂ፡ ሰላማዊ ዜጎች በተከማቹበት ከተማ ትተኩሳለህን? ጄግና በፍጹም እንዲህ ኣያደርግም፡ ተሸናፊና ፈሪ እንጂ። ደርጉ በምጥዋና በሓውዜን ያደረገው የፈሪ ስራ ነበር። ወዳጄ፡ ብልጥግና በወሎ ግንባር በለስ አልቀና ቢለውም አይደል እንዴ የትግራይ ሰላማዊ ዜጎች በሚኖሩበት ከተማ ቦምብ ያዘነበው፡ ታዲያ ከደርጉና ከብልጥግናው ውሳኔ የናንተ ውሳኔ በምን ተለዬ? ብለው ኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች ይጠይቃሉ? :lol:

እዚህ ላይም የረሱትና የዘነጉት ነገር አለ ጀግና አይዋሽም!

በርግጥ ነፍሳቸውን ይማረውንና ጠቅላዪ መለስ ብዙ ጊዜ ሲዋሹ ተደምጠዋል፡ ትዝ ይልዎታል “የኤርትራ ሰራዊት በኢትዮጵያ የለም” ሲሉ፡ ያኔ እንኳ አዲስአበባ ከሻዕብያ ጋር የገባችሁ ግዜ! ትዝ ይልዎታል፤ የተሰረቀውን ስኳር “ተኗል” ሲሉ ወዘተ። “ጀግና አይዋሽም!” የምትለውን ቃል ረስተዋል።

ሥዩም መስፍን በተደጋጋሚ ሲዋሽ ተደምጧል፡ “ባድሜ ለኛ ተወስናለች” ብሎ መንጋውን ሲያስጨፍር ትዝ ይልዎታል። “ጀግና አይዋሽም!” የምትለውን ቃል ረስተዋል።

“ጄግና ኣይሰርቅም” ሕወሓት የተባለ የትግራዮች ባርቲ ከሃገራችን ከኤርትራ መሬት ሰርቆ በአዲሱ ካርታዉ ላይ አስፍሯል፤ ይህ ስርቆት አይደለምን? እስከ ዛሬ ድረስስ የማይታረመው ለምንድን ነው? ጀግና አይዋሽም ጀግና አይሰርቅም!
:mrgreen: