አዲስ አበባ የትግሬ ወያኔዎችን መሳርያ እንደ ችቦ መሰብሰብ ጀመረች- ሌሎች ከተማዎችም ወደ ስራው ገብተዋል።
አዲስ አበባ የትግሬ ወያኔዎችን መሳርያ እንደ ችቦ መሰብሰብ ጀመረች- ሌሎች ከተማዎችም ወደ ስራው ገብተዋል።በነፍስ ወከፍ ታድሎ የነበረው የሽፍታው የጥፋት እና የዝርፊያ መሳርያ ከደሴ ከተማ ትምህርት በመውሰድ በዐመርቂ ሁኔታ መከናወን ተጀምሯል። በተጨማሪም ወያኔ በሁሉም አቅጣጫዎች ቀለበት ውስጥ ገብታ ዶሮ በጋን ሁናለች የሚል ነው። ሌላው ለወያኔ አስደንጋጭ የሆነባት የኤርታራ ሰራዊት ወደ መሃል ትግራይ እያመራ መሆኑና የአማራ ፋኖ በእራሱ ዕዝ በመከላካያ ደረጅ ትጥቅ እና ስንቅ እንድያገኝ ያለው ግፊት ወደ ተግባር ሊገባ መሆኑ ነው። ለወያኔ ይህ ወሽመጥ ቆራጭ እክሎች ይሆናሉ። ግራም ነፈሰ ቀኝ ወደ ሌላ ረጅም የጦርነት ምዕራፍ እየገባን መሆኑን ማመን ያስፈልጋል።