Page 1 of 1

የአቢቹ ምናባዊ..."ጥቁሮቹና ነጮቹ"..... 99.9999% ወደ ተዘጋችው ትግራይ በየት በኩል ገቡ!?

Posted: 02 Nov 2021, 08:41
by sarcasm
የአቢቹ የፈጠራ ገፀ ባህርያት..."ጥቁሮቹና ነጮቹ"....."ሱዳኖቹና ግብፆቹ" 99.9999% ወደ ተዘጋችው ትግራይ በየት በኩል ገቡ!?

የዘፈን ዳርዳሩ እስክስታ እንዲሉ፤ አብይ አህመድ በወሎው ግንባር የውጭ ዜጎች(ነጮችና ጥቁሮች) ከወያኔ ጋር ሆነው ተዋግተው ተሰውተዋል ያለበት ምክንያት ወዲህ ነው።

-ነጮች የተባሉት ግብፆች፣ጥቁሮች የተባሉትም ሱዳኖች መሆናቸውን በቀላሉ መገመት ይቻላል።

አብይ ይህንን ንግግር ያደረገው አማራውን

ከሱዳን ጋር ባለው የድንበር ቁርሾ፤መላው ጦቢያዊን ደግሞ ከአባይ ወንዝ ጋር በተያያዘ ለግብፅ ካለው ጥላቻ ተነሳስቶ "የነገርኩትን በሬ ወለደ ተረት ያምነኛል" ከሚል የመነጨ የንቀት አስተሳሰብ ነው።

አብይ በዚህ በሬ ወለደ ንግግሩ የጦቢያ ህዝብ ልክ በ19ኛው ክፍለ ዘመን ግዜ እንደ ነበረው የአድዋ ጦርነት "ህዝቡ ሆ ብሎ ይነሳል፤ በሚፈጠረው የህዝብ ማእበልም ሂወቴንም ስልጣኔንም አድናለው" የሚል ቀቢፀ ተስፋን ሰንቋል።

ይህንን የአብይን በአለም ላይ ያልተለመደና ወደር አልባ የፈጠራ ውሸት ሰምቶ "ሀገሬ በሱዳንና ግብፅ ተወረረች" ብሎ ወደ እሳት የሚገባ "ሀገር ወዳድ" ይኖር እንደሆን ነገ የምናየው ሆኖ መሬት ላይ በተጨባጭ ያለው ሀቅ ግን አይደለም ሌሎች ብሄርብሄረሰቦች የአብይ ተረት ተረት ሰምተው ወደ ግንባር ሊዘምቱ የወሎ ህዝብም ከረፈደም ቢሆን ነገሩ ገብቶት ፀረ አብይ አህመድ ድምፁን እያሰማ ነው።

እንደ አፋር፣ጋንቤላ፣ቤኒሻንጉልና ኦሮምያ ክልሎች መንግስታትም በቅርቡ በይፋ አብይን ክደው ከትግራይ መንግስትና ሰራዊት ጋር ቆመናል ሲሉ እንሰማቸው ይሆናል። ባጭሩ የአብይ ፀሀይ ጠልቃለች። አብይ እያሰማ ያለው ድምፅ የመጨረሻዋ የጣር ድምፅ ናት።

በነገራችን ላይ👈

-ባጪቲ ባለፈው ሲናገር(ሲተረተር) "ጁንታው ከውጭ ሀገራት መሳርያ የሚያስገባበት እድል 99.9999% ዝግ ነው" ብሎ ነበር።

-ታድያ ኢትዮጵያውያን ያልሆኑ "ነጮቹና ጥቁሮቹ"(ግብፆቹና ሱዳኖቹ) በየት በኩል ወደ ትግራይ ገቡ?
Please wait, video is loading...

Please wait, video is loading...