Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

የመከላከያ ሠራዊት መካነ ሰላም ከተማ ላይ መንገድ ዘግተው መሳሪያህን ስጠን ያሉትን የመካነ ሰላም ወጣቶች ረሽኖ የተዘጋው መንገድ አስከፍቶ በዐባይ አቋርጦ ጎጃም መርጡለ ማርያም ከተማ ደርሷል

Post by sarcasm » 01 Nov 2021, 20:40

#የመርጦለማሪያም_ጀግኖች
#ጀግንነት_እደዚህ_ነው
ከትላንት የቀጠለው የመከላከያና የአማራ ፋኖ ፍጥጫ ከመርጡለ ማርያም ከተማ!
via መነን ንጉሴ

እግሬ አውጪኝ ብሎ ከግንባር እየፈረጠጠ የነበረውን የመከላከያ ሠራዊት መካነ ሰላም ከተማ ላይ መንገድ ዘግተው ከሸሸህ ሽሽ፣ መሸሽ መብትህ ነው። ነገርግን የሃገር ሃብት የሆነውን መሳሪያህን አውልቀህ ስጠን ያሉትን የመካነ ሰላም ወጣቶች ረሽኖ የተዘጋውን መንገድ አስከፍቶ በዐባይ አቋርጦ ጎጃም ጥንታዊቷ መርጡለ ማርያም ከተማ የገባው የሃገር መከላከያ ሠራዊት እንደ መካነ ሰላሙ ገድለኸን አታልፋትም በማለት የበላይ ዘለቀ ልጆች በዚህ መልክ መንገድ ዘግተው ከፈርጣጩ መከላከያ ጋር ሙግት ገጥመው ይተጋተጉ ይዘዋል።

የክልሉ መንግሥት ወደ ቦታው በማቅናት የኾነው ካዬ በኃላ ተመልሶ ለመሄድ ሲል ወጣቱ ለምን አንድ ነገር ሳትሉን የምትሄዱ በማለት መንገዱን ዘግቶ ነበር ነገር ግን አሁን ወደ ባሕርዳር ለስብሰባ ነው የምንሄድ ተጨማሪ ኃይል ይዘን እንመለሳለን በማለት በግድም ቢሆን ሄዷል፡፡




Map - from Mekane Selam, Ethiopia to Mertule Maryam, Ethiopia


https://www.google.com/maps/dir/Mertule ... 10.7512414


Please wait, video is loading...
https://www.facebook.com/wondwossent/po ... 0148298959