ሰበር ዜና፡ የኢትዮጵያ ዝርያ የሌላቸው ነጮች እና ጥቁሮች ከአሸባሪው ቡድን ጋር በጦርነቱ መሳተፋቸዉን ጠ/ሚ አብይ ገለፁ
Posted: 01 Nov 2021, 13:13
"በወሎ ግንባር በነበረው ውጊያ ኢትዮጵያውያን ያልሆኑ ኃይሎች ተሳትፈዋል"፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
በወሎ ግንባር በነበረው ውጊያ ኢትዮጵያውያን ያልሆኑ ኃይሎች ከአሸባሪው ቡድን ጋር መሳተፋቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በጦርነቱ ኢትዮጵያውያን ያልሆኑ እና የኢትዮጵያውያ ዝርያ የሌላቸው ነጮች እና ጥቁሮች ከአሸባሪው ቡድን ጋር ተሳትፈው መስዋትነት መክፈላቸውን ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያረጋገጡት።
የሕወሀት የሽብር ቡድን የከፈተውን ጦርነት እና ጦርነቱን እየመራበት ያለው ህዝባዊ አካሄድ አስመልክቶ ማብራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ህዝብ ለመከላከያ ሠራዊቱ ያሳየው ድጋፍ የሚበረታታ እንደነበር አስታውሰው በቅስቀሳ የመጣውን የህዝብ ኃይል ለማስተናገድ በመንግስት በኩል በቂ ዝግጅት እንዳልነበር፤ አሁን ላይ ከዛ ሁኔታ እርምት ተወስዶ ስትራቴጂካዊ በሆነ መልኩ እየተሰራበት እንደሆነ መግለጻቸውን ኢቢሲ ዘግቧል ።
አጠቃላይ ህዝቡ ለሠራዊቱ ያለው ድጋፍ አሁን ካለው በላይ ሊጠናከር ይገባል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ የገጠመችው ጦርነት ከአንድ ወገን ጋር ብቻ እንዳልሆነ በመረዳት ዋጋ ለመክፈል ያለውን ፍቅር በተግባር ሊገልጽ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያነሱት ዋና ዋና ሀሳቦች የሚከተሉት ናቸዉ፡
በጦርነቱ ኢትዮጵያውያን ያልሆኑ እና ኢትዮጵያዊ ዝርያ የሌላቸው ነጮች እና ጥቁሮች ከአሸባሪው ቡድን ጋር ተሳትፈው መስዋዕትነት ከፍለዋል፤
ኢትዮጵያ የገጠመችው ጦርነት ከአንድ ወገን ጋር ብቻ እንዳልሆነ በመረዳት ህዝቡ ዋጋ በመክፈል ያለውን ፍቅር በተግባር ሊገልጽ ይገባል፤
ጦርነት ማለት የፖለቲካ ማስፈጸሚያ የመጨረሻው ጫፍ ነው፤
የትኛውም ሁኔታ ሊኖር ይችላል ጦርነቱን ግን ኢትዮጵያ እንደምታሸንፍ አትጠራጠሩ ፤
ሚኒስትሮች እና ሚኒስተር ዲኤታዎች መስራት ያለባቸው ጉዳዮች ከጦርነት ትርጉምና ሂደት ጋር የሚያያዝ መሆን አለበት፣
የበላይነት የገዢነት የአዛዥነት በሽታ የተጠናወተው ቡድን በምርጫ እንደማይሳካለት አይቶታል ፣ በዴሞክራሲ መንገድም አይቶታል፣ አሁን የመጨረሻ መንገድ የሚከፈለውን ዋጋ ከፍለን ማዘዝ መግባት ማፍረስ አለብን በሚል የገባበት መምገድ ነው፤
ይህ ቡድን ሌባ ነው፣ ታሪክ ይሰርቃል ፣ቅርሰ ይሰርቃል፤ የሌብነት ሂደቱ አዲስ አይደለም፣
የዛሬዋ ኢትዮጵያ ምንም ጦርነት ሳታደርግ ይህንን ኃይል ብትቀበለው የትላንቱን ህወሓት ሳይሆን የዘመነውን ለመሸከም ጫንቃዋ አይችልም ፣
የኢትዮጵያ ህዝብ ባርነትን አልቀበልም ማለቱ መልካም ነው፣
በወሎ ግምባር በነበረው ውጊያ ኢትዮጵያዊያን ያልሆኑ ኃይሎች ተሳትፈውበታል፣ መስዋትነት ከፍለዋል፣ ነጮች ጥቁሮች በደሴ ውጊያ ሞተዋል፣
ኢትዮጵያዊ የሆነው ሰው ሀገሩን ለማዳን ምን ያህል ዝግጁ ነው፣
ጥቅምት 22/2014, አዲስ አበባ
ጤና፡
የልብ ድካም መንስኤዎችና መከላከያ ወሳኝ መንገዶች። ለጥንቃቄ መታየት ያለበት። መፍትሄዉ በእጃችን ነዉ:: ለማየት ሊንኩን ወይም ምስሉን ይጫኑ