Page 1 of 1

"ቦምቡንም ሆነ የዘር ፍጅት የሚያነሳሱትን በሽተኞች ለማስቆም የትግራይ መከላከያ ሃይል ቢሾፍቱንና አዲስ አበባን በቶሎ መቆጣጠር አለበት።" ያሬድ ጥበቡ

Posted: 01 Nov 2021, 12:57
by sarcasm
ተጻፈ በያሬድ ጥበቡ

ኢህአዴግ አዲስ አበባ ሊገባ ቀናት ቀርተውታል:: ዳዊት ዮሐንስ ጋ ስልክ ተደወለ:: ደዋዩ የአሜሪካ ብሄራዊ ደህንነት ባለሥልጣን ነው:: "ሠራዊታችሁ ወደፊት እንዲገሰግስ አንፈልግም: ባላችሁበት ቁሙ" ይለዋል:: ዳዊት አበደ :: ማን ብትሆን ነው አንተ ቀጭን ትእዛዝ ልትሰጥ ምትሞክረው: ይህ እኮ የህዝቦች መራራ ትግል ውጤት ነው: አይመለከትህም: አያገባህም ብሎ ጆሮው ላይ ዘጋበት::

መለስና ተስፋዬ ዲንቃ ለንደን ላይ አንድ አዳራሽ እያሉ የኢህአዴግ ጦር ቦሌ አየር ማረፍያን ተቆጣጠረ:: አደራዳሪው ሄርማን ኮኸን የምንተእፍረቱን "የኢህአዴግ ሠራዊት አዲስአበባ እንዲገባ ተስማምተናል" ብሎ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጠ::

ዛሬ ከ30 ዓመታት በሗላ ታሪክ ራሷን እየደገመች ይመስላል:: አሜሪካ የትግራይ መከለከያ ሃይል ወደፊት እንዳይገፋ እያስጠነቀቀ ነው:: ሃገራዊ ሁኔታው ግን ፍፁም የተለየ ነው:: ትግራይን በቦምብ የሚያጋይ ፈሪና ጨካኝ መንግስትና: ትግሬዎችን ግደሉ: አፍኑ: እሰሩ የሚሉ የማህበራዊ ሚዲያ የአቢይ ገረዶች ድምፃቸውን ከፍ አድርገው የሚጮሁበት ወቅት ነው:: ከ30 ዓመቱ በፊት የተለየ አሁናዊና ግልፅ አደጋ አለ:: ቦምቡንም ሆነ የዘር ፍጅት የሚያነሳሱትን በሽተኞች ለማስቆም የትግራይ መከላከያ ሃይል ቢሾፍቱንና አዲስአበባን በቶሎ መቆጣጠር አለበት:: ይህን ለአሜሪካኖቹ አስረድቶ ወደፊት መመረሽ የግድ ነው:: ቦሌ ሲደረስ ቡራኬያቸውን መስጠታቸው አይቀርም:: [/b]

እስከዝያው ከመበታተንና ሽንፈት የተረፈም የመከላከያ ሠራዊት ካለ የአቢይን የቀቢፀ ተስፋ ጩኸት ሰምቶ ተጨማሪ ጥፋት ከሚያደርስ አቢይን ወደ ስዊዘርላንድ ቤተሰቡ ጋ እንዲቀላቀል ሸኝቶ ከህወሓት ጋ ለመደራደር ቢተጋ ተገቢ መስሎ ይታየኛል::
Please wait, video is loading...