Page 1 of 1

ጦርነቱ የአማራ ብድር እና ቁጠባ ተቋምን ከ6 ቢሊዮን ብር በላይ አክስሯል - የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም ዋና ሥራ አስፈፃሚ

Posted: 01 Nov 2021, 09:07
by sarcasm
ጦርነቱ የአማራ ብድር እና ቁጠባ ተቋምን ከ6 ቢሊዮን ብር በላይ አክስሯል ፤ ተቋሙ

የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም በአማራ ክልል እተካሄደ ባለው ጦርነት ምክንያት ከ6 ቢሊዮን ብር በላይ ኪሳራ እንዳጋጠመው አስታወቀ። ከ60ሺህ በላይ የተቋሙ የብድርና ቁጠባ ደንበኞችም ለከፍተኛ የኢኮኖሚ ቀውስና መፈናቀል መዳረጋቸውን ገልጿል። ደሴ የሚገኙ አንድ የተቋሙ ተፈናቃይ ደንበኛ አሁን በተፈጠረው ወቅታዊ ሁኔታ መና መቅረታቸውን ተናግረዋል።

የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መኮንን የለውምወሰን በጽ/ቤታቸው ለዶይቼ ቬለ እንዳሉት የሕወሓት ኃይሎች በወረራ ይዘዋቸው በነበሩ አልያም በቆዩ አካባቢዎች የሚገኙ ጽ/ቤቶችን ንብረት በከፍተኛ ሁኔታ ዘርፈዋል አልያም አውድመዋል፤ ብለዋል፡፡

አሁን ነፃ በሆኑ ከ90 በላይ በሚገኙ ጽ/ቤቶች ላይ በተደረገ የዳሰሳ ጥናት መሰረት ከአንድ ቢሊዮን በላይ የሚገመት ንብረት መዘረፉን አቶ መኮንን ገልፀዋል፡፡
ተቋሙ በጦርነት ቀጠና የሚገኙና በጦርነቱ የተፈናቀሉ ከ60ሺህ በላይ ደንበኞች እንዳሉት ያመለከቱት ዋና ስራ አስፈፃሚው፣ አጠቃላይ በነዚህ ደንበኞች እጅ የሚገኝ 5 ቢሊዮን ብር ለብክነት መዳረጉንና ይህም ለተቋሙ ከፍተኛ ክስረት አንደሆነ አስረድተዋል፡፡

Continue reading https://www.dw.com/am/%E1%8C%A6%E1%88%A ... a-59652406