Page 1 of 1

Entire Amhara Region put under curfew from 8pm in the evening! በሁሉም ከተሞች ከምሽቱ 2፡00 በኋላ እንቅስቃሴ ማድረግ አይቻልም!

Posted: 31 Oct 2021, 14:24
by sarcasm
ከአማራ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት የተላለፈ አስቸኳይ ጥሪ

የትህነግ አሸባሪና ወራሪ ኃይል በአማራ ክልል ሕዝቦች ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት እየፈፀመ ህዝቡን እየገደለና እያዋረደ፤ ንብረቱን እየዘረፈ፣ እያወደመ እና ኢትዮጵያን ለማፍረስ የመጨረሻ የሞት ሽረት ትግል እያደረገ ነው፡፡ ይህንን በተጨባጭ እየገጠመን ያለውን የሕልውና አደጋ ለመቀልበስ በመደበኛው የሕግ ማስከበር ሥርዓት ብቻ ማሸነፍ የማይቻል ሆኖ በመገኘቱ፤

የአማራ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት ጥቅምት 21 ቀን 2014 ዓ.ም ባካሄደው 6ኛ ዙር፣ 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ አስቸኳይ ስብሰባ የሚከተሉትን የአስቸካይ ጥሪ ውሳኔዎች አስተላልፏል፡

1. ከሚሰጡት አገልግሎት አስፈላጊነት አኳያ እየተመዘነ የሚወሰን መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ማንኛውም የመንግስት ተቋም መደበኛ አገልግሎቱን አቋርጦ በጀቱን ጨምሮ ሁሉንም ነገር የገጠመንን የህልውና ዘመቻ ለመቀልበስ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ እንዲረባረብ ተወስኗል፣
2. ሁሉም የመንግስት ተሸከርካሪ ወደ አንድ ማዕከል በማሰባሰብ ለሕልውናው ዘመቻ አገልግሎት እንዲውል እንዲደረግ፣
3. የግል ተሸከርካሪ ባለቤቶች ለሕልውና ዘመቻው ስኬት ሲባል በተፈለገ ጊዜ ሁሉ ተሸከርካሪዎቻቸውን በመስጠት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ተወስኗል፣
4. በየደረጃው የሚገኝ አመራር የሕልውና ዘመቻውን ተቀብሎ የሚሰለፈውን ሕዝብ አደራጅቶ ከፊት ሆኖ እየመራ ወደ ግንባር እንዲዘምት ይህን በማያደርጉ አመራሮች ላይ ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ተወስኗል፣
5. ሁሉም የመንግስትና የግል የጦር መሳሪያ የታጠቀ በሙሉ ለሕልውና ዘመቻው አገልግሎት እንዲውል ተወስኗል፡፡ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ማንኛውም የግል መሳሪያ የታጠቀ የክልሉ ነዋሪ በማንኛውም ምክንያት በሕልውና ዘመቻው ላይ የማይሳተፍ ከሆነ የታጠቀውን የግል መሳሪያ በአደራ ለመንግስት እንዲያስረክብ ወይም እድሜው ለትግል ለደረሰ እና አካላዊ ጤንነት ላለው ለቤተሰብ አባሉ ወይም ለሌላ ሰው በማስተላለፍ ለህልውና ዘመቻው አገልግሎት እንዲውል እንዲያደርግ፣
6. በደጀንነት የሚገኘው ሕዝባችን ለሕልውና ዘመቻው የሚያስፈልገውን የሎጂስቲክስ አገልግሎት በማቅረብ የሕልውና ዘመቻውን ውጤታማ እንዲያደርግ፣ በየደረጃው የሚገኘው አመራርም አቅርቦቱ የተሳለጠ እንዲሆን አስፈላጊውን እንዲፈጽም ተወስኗል፣
7. የሕልውና ዘመቻውን ተቀብሎ በግንባር ለመፋለም ከሚሰማሩት ውጭ ያለው ማንኛውም የክልሉ ነዋሪ በየአካባቢው ተደራጅቶ የአካባውን ጸጥታ እንዲጠብቅ፣ ጸጉረ ለውጦችንና ሰርጎ ገቦችን እንዲከታልና ለሕግ አስከባሪ አካላት አሳልፎ እንዲሰጥና ለሕልውና ዘመቻው የበኩሉን ኃላፊነት ሁሉ እንዲወጣ፣
8. የህልውናውን ዘመቻ ውጤታማ ለማድረግ በሚደረገው እንቅስቃሴ ላይ ለትግሉ በተለያየ መንገድ እንቅፋት በሚሆን ማንኛውም ሰው ወይም ቡድን ላይ በየደረጃው እየተወሰነ የጸጥታ አካሉ አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስድ ተወስኗል፣
9. የተለያዩ አገልግሎቶችን እንዲሰጡ ከተፈቀደላቸው ተቋማት ውጭ በሁሉም ከተሞች ከምሽቱ 2፡00 በኋላ እንቅስቃሴ ማድረግ አይቻልም፣
እነዚህን ዘጠኝ አስገዳጅ ውሳኔዎች ዝርዝር አፈጻጸም በተመለከተ በክልል ደረጃ በተቋቋመው የዘመቻ መምሪያ በሚቀመጥ አሰራር የሚወሰን ይሆናል፡፡

ጥቅምት 21 ቀን 2014 ዓ.ም
ባህር ዳር
Please wait, video is loading...

Re: Entire Amhara Region put under curfew from 8pm in the evening! በሁሉም ከተሞች ከምሽቱ 2፡00 በኋላ እንቅስቃሴ ማድረግ አይቻልም!

Posted: 31 Oct 2021, 14:44
by tolcha
Viva-Aschenaqiw, Tigaru!!!