ወደ ደሴ ሾልከው የገቡ የአሸባሪው ሕወሓት አባላት እንዳልነበር እየሆኑ ነው ! October 31, 2021 – Konjit Sitotaw
Posted: 31 Oct 2021, 02:21
https://mereja.com/amharic/v2/616003
so much for Desee !Desse !
“በየቦታው የሽብር ቡድኑ ሰርጎ ገቦች አስከሬን ተበትኗል” ያሉት የፀጥታ ተቋማት ምንጮቻችን “ደሴ አሁን ላይ አንፃራዊ ሰላም ላይ ናት፤ ጀግኖቹ ሥራ ላይ ናቸው” ሲሉ አክለዋል። ሕዝቡ በሃሰተኛ መረጃዎች ሳይሸበር ለመከላከያ ሰራዊትና አብረውት ለተሰለፉ የፀጥታ ኃይሎች ደጀን በመሆን እንዲቀጥል፤ በዚህም ኅልውናውን እንዲያስጠብቅና የሽብር ቡድኑን ሕወሓት ዕድሜ እንዲያሳጥር ተጠይቋል።
–
ይህ በእንዲህ እንዳለ የአማራ ክልል መንግሥት የፌደራል መንግሥቱን ጥሪ በመቀበል ማምሻውን ባወጣው ሕዝባዊ የክተት ጥሪ በክልሉ የሚኖሩና ሁኔታና አቅማቸው የሚፈቅድላቸው አገር ወዳዶች ሁሉ በሕዝባዊ ማዕበል የመጣውን ወራሪ ኃይል ለመደምሰስ እስከ ጥቅምት 23 ስንቅና ትጥቅ በመያዝ በየወረዳ ማዕከላቱ እንዲገኙ ጥሪ አቅርቧል።
–
የሐረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲም በተመሳሳይ ነዋሪው ለሕዝባዊ ትግል እንዲዘጋጅ ጥሪ አቅርቧል። የፌደራሉ መንግሥት ኢትዮጵያዊያን ከሽብር ቡድኑ ፕሮፖጋንዳ ራሳቸውን አቅበው ቡድኑን እስከወዲያኛው ለመቅበር እንዲተጉ ጠላት የከፈተው ጦርነትም የግንባር ብቻ ሳይሆን የምጣኔሃብትም ጭምር መሆኑን ተረድተው እንዲመክቱ መጠየቁ ይታወሳል ሲል ዋልታ ዘግቧል።