Page 1 of 1
የአገሪቱ ገበያ ምን ይመስላል? የላስቲክ ቤቶች የመፍረስ ምልክት እየታየ ቢሆንም ... መፍረስ አለበት
Posted: 09 Oct 2021, 10:02
by Abaymado
በቅርብ ግዜ አዲስ አበባን ያጥለቀልቀው በላስቲክ ቤት የተወጠሩ ንግድ ቤቶች ናቸው:: መንግስት ምን ይጠብቃል? ይህ ግዜ ከተሰጠው መዘዙ ቀላል አይሆንም:: በአሁኑ ሰዓት ሁሉም እየወጣ ላስቲክ መወጠር ጀምሯል:: የማታ ማታ ቦታው የኛ ነው ማለታቸው አይቀርም::
አንደኛ የከተማውን ውበት እያበላሸ ነው:: ሁለተኛ በህገወጥ መንገድ ለመክበር መፈለግ ነው:: ማን ይቀራል : ሁሉም መውጣቱ አይቀርም:: መንግስት ማፍረስ አለበት::
Re: የአገሪቱ ገበያ ምን ይመስላል? የላስቲክ ቤቶች የመፍረስ ምልክት እየታየ ቢሆንም ... መፍረስ አለበት
Posted: 09 Oct 2021, 10:24
by Abaymado
የሽንኩርት ዋጋ ከ 48 ብር ወደ 30 ብር ወርዷል::
እንቁላል አሁን እየተሸጠበት ያለው ዋጋ 8 ብር ነው:: እንዴት ሊሆን ይችላል?
ይህ ከውጭ የሚመጣ ነግር አይደለም:: ህዝባችን በጣም ሰነፍ ሕዝብ ነው:ዶሮ ማርባት መልመድ አለበት:: ገጠር ያሉ ሰዎችስ ምን እያረጉ ነው? ይሄ አንድ ሊባል ይገባዋል::
ሙዝ እስካሁን ጥሩ የሚባል ማግኘት አልተቻለም:: ሙዙ ተበላሽቷል:: ምክንያት ምንድነው? መንግስት ሊከታተለው ይገባል: በተለይ ግብርና ሚንስቴር::
ቀደም ብዬ እንዳልኩት ሌሎች አገር የሚበቅሉ እህሎችን ወይም አትክልቶችን አገራችን አምጥታ ማራባት አለባት:: coconut በጣም የሚፈለግ ነው:: ለቸኮሌት የሚሆነው cocoa:
ለጤና በጣም ተፈላጊው አረንግዋዴ ሻይ ለሕዝቡ በየሱቁ ቢሸጥ አሪፍ ነው:: ቀዩን ሻይ ቀንሶ አረንግዋዴውን በከፍተኛ ደረጃ ማምረት ነው::
በምዕራብ አፍሪካ የሚገኘው cassava እዚህ ቢራባ ጥሩ ነው :: እርሃብን ለመከላከል ይረዳል::
በጣም ቀላል የማይባሉ ለጤናጠቃሚ የሆኑ የአትክልት ዝርያዎች አገራችን ላይ የሉም:: ምን እንጠብቃለን?