ምናልባት ኢሳያስ በአብይ ሳይከፋ አልቀረም:: ግምት: ለምን መከላከያ ከመቀሌ ወጣ የሚል ይመስለኛል:: በተጨማሪ ኤርትራ ያለፍላጎቷ ተገዳ ከትግራይ ስለወጣች ተበሳጭተው ሊሆን ይችላል:: የ ER የሻብያ ቃል አቀባዮች ይህን የሚያቁ ይመስለኛል::
ሹመቱን በተመለከተ ቀድሞ ማን እንደሚመረጥ ደርሶን ነበር:: ብርሃኑ ነጋ የትምህርት ሚንስቴር ሁን ቢባል አሻፈረኝ እንዳለ ነበር የተነገረው:: ደመቀ መኮንን ያለምንም ጥርጥር ቦታውን እንደማይለቅ የታወቀ ነው:: ምክንያቱም አሁን አገሪቱ ባለችበት ሁናቴ አገሪቱን እየወከለ ያለው እሱ ነው:: ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ምንም ዋጋ የሌለው ቦታ ነው:: የውጭ ጉዳይ ቦታው ይገባዋል::
ግን ግን ግራ የገባኝ ዛሬም እንደገና አብይን እጩ አድራጊው እሱ መሆኑ ነው:: እስከመቼ?
የአብን ሊቀመንበር ቦታ አሪፍ ቦታ ነው:: ያለቦታው የሚባል ነገር አይገባኝም:: እስካሁን የገቡት ምን አረጉ?
የብርሃኑ ነጋ ቦታ ብዙው የሚጠብቀው የኢኮኖሚ : የገንዘብ ሚንስቴር ወይም የባንክ ገዢ ።። ነበረ:: እኔ በበኩሌ ትምህርት ሚንስቴር ጥሩ ቦታ ነው:: ምን ለውጥ ያመጣል የሚለውን እናያለን:: ብቻ ተዝፍዝፎ ግዜውን ጨርሶ እንዳይወጣ እፈራለሁ ::
እንደሚመስለኝ የአገሪቱን የትምህርት ፖሊሲ ብትንትኑን ማውጣት ነው::
የመከላከያ ሚንስትር ጥሩም መጥፎም ጎን አለው:: ጥሩ ጎኑ ይህ ቦታ አማራ እና ኦሮሞ የሚፋጩበት በመሆኑ ነው:: ጉዳቱ ምን ሊያረግ ይችላል? ግራ ያጋባል::
በተረፈ እዛው የነበሩ እዛው መሸጋሸግ ነው ያለው : ቢቀየሩ ጥሩ ነበር::
የተረሳው ነገር: የውሃ ሚንስትሩ ስለሺ በቀለ ጉዳይ : ፊት መጠበቁ ይሻላል::