ይህ ሁሉ ዝርዝር ከመዋቅር ውጭ ባለ ሰው አይሰራም። ከስር የሚታየው ዝርዝር ለብልፅግና ካልሆነ በማንም ሊወጣ አይችልም። የአመራር ዝርዝር ቋት ውስጥ ሰርተው ኤርሚያስ ሸውደውት መሆኑ ነው። የአመራር ቋት አማራጭ ውስጥ አውጥተው፣ ከዋናው አማራጭ ውጭ የተሰራውን አማራጭ በሰው በሰው ሲልኩለት እውነት መስሎት መሆን አለበት። የሕዝብ ትርታ መለኪያ አድርገውት መሆኑ ነው። የሀሰት መረጃ አሰራጭተው አጀንዳ ሰጭ አደረጉት። ኤርሚ ሆዬ አንዱ ሲልክለት ቀበል አድርጎ ሊሞገስበት ለጠፈው!
ኤርሚያስ በለጠፈው መሰረት ብዙ ሰው በውስጥ መስመር ተጋርቶታል። እየተደዋወለ ተነጋግሮበታል። ሴራ እተነትናለሁ የሚለውን ሰውዬ ሴራ ሰሩበት። ሕዝብን አወናበደበት። በአጭሩ ኤርሚያስን የሴራቸው ተባባሪ አደረጉት። የብልፅግናን ሴራ ተቀብሎ ሕዝብን በማወናበድ ሰራላቸው።
አንዱ በሴራ ያሾለከለትን ብንገምት ብሎ ለጥፎታል። ግን ይሄን ዝርዝር እሱ ሊሰራው አይችልም። ይህ ዝርዝር ሆን ተብሎ በሴራ የሾለከለትና ጉድ የተሰራበት እንጅ የራሱ ሊሆን አይችልም። ለዛም ነው ከሆነ ጊዜ በኋላ ደብቆት ነበር።

