Page 1 of 1

በሰሊጥ ኣርበኞች የሚሽከረከር የኢትዮጵያ ፖለቲካ - የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ 'በተወሰኑ አካባቢዎች ለሚገኙ የሰሊጥ አምራቾች' ብቻ ብድር ፈቀደ

Posted: 05 Oct 2021, 20:36
by sarcasm
ብሔራዊ ባንክ አውጥቶት የነበረውን የብድር ገደብ ማሻሻያ አደረገበት።

=======================
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በቅርቡ ከብድር አቅርቦት ጋር በተያያዘ የጣለውን እገዳ ማሻሻያ ማድረጉን አስታውቋል፡፡
በማሻሻያው ባንኮች አምስት የብድር ዓይነቶችን መፍቀድ እንደሚችሉ ታውቋል፡፡ እነዚህም ባንኮች የሰጡትን ብድር ለማስመለስ ሐራጅ ያወጧቸውን ንብረቶች ለመግዛት ለሚጠይቁ ገዥዎች ብድር፤በሁለተኛና በሦስተኛ ወገኖች መካከል የሚደረግ ግብይትና ለባንክ ሠራተኞች የሚሰጥ አስቸኳይ ብድር፤ቅድመ ሁኔታዎችን አሟልተው የመኖርያ ቤት ለመግዛት ወይም ለመገንባት ከታመነባቸውና ከፀደቁ ድርጅቶችና ከተቋም ሠራተኞች ለሚቀርቡ የብድር ጥያቄዎች እና በተወሰኑ አካባቢዎች ለሚገኙ የሰሊጥ አምራቾች ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለባንኮች ባስተላለፈው መልዕክት ከላይ የተዘረዘሩት አምስት የብድር ዓይነቶች ላይ ብድር መስጠት እንደሚችሉ አስታውቋል።


Please wait, video is loading...