የእኔም ጉዳይ ቦሌ ሠፈር ውስጥ የደረሠብኝን ግፍ ይመለከታል፡፡
ወሰንግፋ ድንበሩ ከአብበሲንያ ከአያቱ በኃላ የመጣ የጭቃ ሹም ልጅ ና ጎረቤቴ ነው፡፡ በደርግ ጊዜ ወደ ወለጋ ሄደው እንዲሠፍሩ ከተደረጉት ፋርጤዎች አምልጦ መጥቶ ነበር በእኔ አጠገብ መሬት ተሰጥቶትና ቤት ሠርቶ ጎረቤቴ የሆነው፡፡ ታዲያ ይኀውላችሁና ጉድ ሰራኝ፡፡ ኮለኔል አብይ ፋርጤ ነው ብሎ ማን እንደነገረው እኔ አላውቅም፡፡ በሌሊት ተነስቶ ድንበር ጥሶ፣ አጥረን አፍርሶ ሌላ አጥር ሰርቶ አደረ፡፡ ያው በጨረቃ ሰራው ማለት ነው፡፡
ጠዋት ይህ መሆኑን አይቼ ወደ ፍርድቤት ሂጄ ሁከት ይወገድልኝ ብዬ ማመልከቻ አቀረብኩ፡፡ ፍ/ቤቱ ገና ስሜን ሲያይ ማመልከቻህን አስተካክለህ አምጣ አለኝ፡፡ ስሜ እኮ ያው በዳዳ ጀባዳ ነው: ጉዳዬም አጣዳፊ ነውና እባክዎን ማገጃ ይጻፉልኝ አልኩት፡፡ ስምህን እያነበብኩ ጊዜ ከምፈጅብህ እንዲጣደፍልህ ከፈለግህ ቀይረህ አምጣው አለኝ፡፡ ታዲያ ማን ለበል አልኩት፡፡ ብዙ ናቸው ግን ወለተ-ዳንኤልም ማለት ትችላለህ አለኝ፡፡
እኔን ደግሞ ፍ/ቤት ፍትህ ነፈገኝና እነሆ እጮሀለሁ፡፡
በመሆኑም በየቢሮክራሲው ሠፋሪዋች በዝተዋልና እንዲቀነሡ Ethio 360ዎች ለአቤቤ አዲስ አበቤ ማመልከቻዬን ብታቀርቡልኝ፡፡ zeHabeshan ና ESAT ብትተባሩዋቸው?
በእንግልዚኛ ከጻፍኩት እናንተም ቁቤ ይመስላችሁና ማመልክቻዬን ትጥሉብኛላችሁ ብዬ ነው በሳባ ፊደል ኮሚዩተሬን ሰነጥኩት፡፡ ይቅርታ!