Page 1 of 1

የራስን ችግር በራስ መፍታት ፍልስፍና

Posted: 28 Sep 2021, 11:50
by Horus
የሀው የአለም ቅኝ አገዛዝን ለመታገር ገንኖ የነበረው የራስን እድል በራስ መወሰን ፍልስፍና በአዲሱ ቅኝ ግዛት ተጠልፎ የብሄር፣ ብሄረሰቦች መገነጣጠልና የከፋፍሎ መግዣ መሳሪያ ከሆነ ወዲህ ያ ቲኦሪ ረክሶ የጎሳ ፖለቲካ ማጨማለቂያ ሆኖ ነበር ።

አሁን ዘመናዊ ቅኝ ገዦችን ከጣልቃ ገብነት ለማባረር አፍሪካዊያን የራስን እድል በራስ መወሰን ይባል የነበረው ጸረ ኮሎኒያል ፊሎሶፊ የራስን ችግር በራስ መፍታት በሚለው ትልቅና አዎንታዊ ፍልስፍና ተተክቷል!

ኢትዮጵያና ኤርትራ ይህን አዲስ ንቅናቄ እየመሩት ይገኛል

ሱዳንም የራሷን ችግር በርሷ እንድተፈታ ለቀቅ ትደረግ !

የደስታ መስቀል !