ሆረስ ነኝ፤ ክቡር ገና ለምን ዛሬ ተናደደ?
Posted: 21 Sep 2021, 23:27
እኔ የዚህን ሰውዬ የፖለቲካ ህይወት ታሪክ አላውቀውም ። ግን አንድ ግዜ በተናገረው አባባል በጣም አሮጋንትና ሙሉ ህሳቤና ሎጂክ ሳያሰላስል ትላልቅ መደምደሚያዎች መወርወር የሚወድ ቀብራራ ይመስለኛል ። ወደ ዛሬ አመት አካባቢ የትግሬ ጦርነት ከመጀመሩ በጣም ቀድሞ አቢይ ፓርኮች እያሰራ አበባ ያስተክል ነበር። በዚያን ወቅት ኢቲዮቴሌኮም ፕሪቬታይዘድ ይደረግ አይደረግ ውይይት/ክርክር ነበር ። በትክክል የማስታውስ ከሆነ የኢዜማ ፓርቲ ባብዛኛው ብርሃኑን ጨምሮ ሃሳባቸው ወደ መቃወም ወይም ቀስ ብሎ በመወሰን ላይ ያጋደለ ነበር ። እንደዚህ ያለ ብሄራዊ የኢኮኖሚ ሆነ ሌላ ፖሊሲ ላይ ፓርቲዎች የመሰላቸውን አቋም ቀርጸው መከራከር እጅግ ስልጡን ባህሪ ነው ። እኔ ክቡር ገናን በጣም የታዘብኩትና ለኢዜማ አክሳሪ ሰው እንደሆነ የደመደምኩት የሚከተለውን ያለ ግዜ ነው ። "አቢይ ቴሌኮም ለግል ባለሃብቶች ሊሸጥ የሚቻኮለው ብሩን ምን ሊያደርግበት ነው? አበባ ሊተክልበት?" አለ ። ያኔ ነበር የሚናገረውን የማይመጥን ስለአንድ ነገር ሙሉ ህሳቤ የማያደርግ አሮጋንት ሰው ብዬ የዘጋሁት ።
አሁንም ቢሆን የትግሬ ጦርነት ድፍን 10 ወር ከሆነው በኋላና ምናልባትም እንደ አምላክ የሚያየው አሜሪካን በኢትዮጵያ ላይ ሲዘምት ለምን ሲል ዛሬ ይህን ትችት ያቀረበው? ለምንድን ነው ባለፉት 10 ወራት ያልተቸው? ፕሮፍ፣ ብርሃኑ በቡልቡላ የጦር ምርቃት ላይ ስለተገኘ ነውን? ወይስ በመስከረም 24 በሚውለው ያቢይ ስልጣን ርክክብ ክቡር ገና ምንም የመንግስት ስልጣን ስላልተሰጠው? እውነቱ በቅርብ አንድ የሆነ ሶሺያ ሚዲያ ያወጣዋል ።
እኔ ግን እንደማይመቸኝ የተገነዘብኩ የዛሬ አመት ነው ። ዛሬም ቢሆን የሚቀባጥረው ትችት ሙሉ ሚዛን የሜለው እና ስለሚሊታሪ ልምድ ሆነ በአንድ ጦርነት ሙሉ ሂደት እና እስትራተጂ ውስጥ ከግዜ ወደ ግዜ የሚፈጠሩት የጦርነት ውጣ ውረድ ዳይናሚክስ ዜሮ እውቀት ያለው ሰው ይመስለኛል ። የጦር አዛዦች አይሳሳቱም ማለቴ አይደለም ፣ አንድ ሙሉ ጦርነት ቀርቶ አንድ ዉጊያ ትክክል ነው ስህተት ብሎ ለመተቸት በቂ ወታደራዊ ትንተና እና ፋክቶች በመስጠት እንጂ አንድ ሰው አዲሳባ ቡና እየጠጣ ጦርነቱ በሱ ምኞት ፍጥነት እንዲቀላጠፍለት የሚቀላምድ ሰው እኔ ጉዳይ ብዬ አላነበውም። የትግሬ ጦርነት የተራዘመበት ምክኛቶች አሉት! እነዚያን ምክኛቶች ክቡር ገና አያውቃቸውም።