Page 1 of 1

በሱዳን እየተካሄደ ያለው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ግብፅን ጭምር ስጋት ላይ የሚጥል ነው ተባለ

Posted: 21 Sep 2021, 09:45
by Abdisa
በሱዳን የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ተካሄደ

On Sep 21, 2021



የሱዳን መንግስት ላይ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ መካሄዱን የሀገሪቱ መንግስት ሚዲያ አስታውቋል።

በተለያዩ ሚዲያዎች አሁን እንደተዘገበው ማንነታቸው ያልተገለጸው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ያደረጉ አካላት በካርቱም ኦምዱርማን የሚገኙትን የሀገሪቷን የሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ለመቆጣጠር ሙከራ ማድረጋቸውም ነው የተገለፀው፡፡ መንግስት ሁኔታውን ለመቆጣጠር ጥረት እያደረገ መሆኑን አስታውቋል።

በአሁኑ ሠዓት ታንኮች ወደ ኦምዱርማን ድልድይ እና ወደ ሀገሪቷ ፓርላማ ህንፃ ተጠግተው መንገዱን በመዘጋት እንደተቆጣጠሩት ሲገለፅ በአካባቢው የጸጥታ አካላት እንደተሰማሩም ነው የተመላከተው፡፡

በካርቱም የሱዳን የጸጥታ አካላት ናይልን ከኦምዱርማን የሚያገናኘውን ድልድይ ቢዘጉም፣ በአካባቢው ሁኔታዎች ተረጋግተው እንቅስቃሴዎች እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ መቀጠላቸው ነው የተሰማው፡፡





Re: በሱዳን እየተካሄደ ያለው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ግብፅን ጭምር ስጋት ላይ የሚጥል ነው ተባለ

Posted: 21 Sep 2021, 10:24
by Abdisa
የሱዳኑ ጁንታ እሳት ለኩሶ ከዳር ሆኖ መመልከት ወይም ቁጭ ብሎ መሞቅ እንደማይቻል ከህወሓትና ድርጊቱ መማር አለበት።


Re: በሱዳን እየተካሄደ ያለው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ግብፅን ጭምር ስጋት ላይ የሚጥል ነው ተባለ

Posted: 21 Sep 2021, 13:09
by Digital Weyane
ጁንታው ዎንድሜ eden/Sarcasm ስልክ ደውሎ በሱዳን የተሞከረውን መፈንቅለ መንግስት <<ኡኔ ነው ያከሸፍኩት!>> ብሎ ሲነግረኝ እጅግ ከመገረሜ የተነሳ ማመን እንኳ ተስኖኛል። ዎደ ውጭ አገር የሸሹ ጁንታ ዎገኖቼ ከኢትዮጵያ ህዝብ በዘረፉት ብር ሃምበርገር ኡየጎመጡ፣ ዊስኪ ኡየተጎነጩና፣ እስትሪፕ ክለብ ኡያደሩ እጅግ የሚያስገርሙ በርካታ ታላላቅ ተግባራትን ይፈፅማሉ ብዬ አልጠብቅም ነበር። አይ ዎዝ ሮንግ! :roll: :roll: