አሁን አገሪቱ ውስጥ ግብርና ሚንስቴር አለ የሚባልበት አገር ላይ አይደለንም:: ቢያንስ ቢያንስ በምግብ ራሳችንን ቻልን ተብሎ በሚሰበክበት ሰዓት ያሉን የምግብ እህሎች እስከነጭራሹ ብልሽትሽታቸው እየወጣ ነው::
ጥሩ ሙዝ በአሁኑ ሰዓት እዚህ አገር ላይ ማግኘት ዘበት እየሆነ ነው:: በጣም ቀጫጫ: ሲያዩት የሚያስጠላ ሙዝ ነው ያለው:: መንግስት የዚህን ችግር ለማጥናት ሞክሯል?
ቡርትካንማ አይታሰብም:: በፊት በሁለት ብር ሁለት ኪሎ ምን የመሰለ ቡርትካን ይገዛ ነበር:: አሁን 60 ብር ተከፍሎ የሚገኘው ለዛውም ከተገኘ አንድ ኪሎ ሎሚ ሎሚ የሚል ቡርትካን ነው:: መንግስት የዚህን የቡርትካን መጥፋት ምክንያትስ ያጠና ይሆን?
ሌላው ደሞ የሚገርመው ነገር ጤፍ ከኢትዮጵያ ውጥቶ ሌላው አገር እየበቀለ ሲሆን: ኢትዮጵያ ግን ሌላው አገር ብቻ የሚበቅለውን አምጥታ ማብቀል እንደ ውርደት የምትቆጥር አገር ትመስላላለች:: ምንድነው ችግሩ?
ለምሳሌ cassava እኛ አገር መኖሩን እጠራጠራለሁ: ለምን የለም? ይህ አገራችንን የሰውን አገር እርዳታ ከምትጠባበቅ ይገላግላት ነበር:: ካሳቫ ለሁሉ ነገር የሚሆን ምግብ ነው::