Page 1 of 1

ጉራጌ ሰንደቅ አላማውን መለወጥ አለበት!! ክልሎች ሁሉ ባንዲራቸውን መቀየር አለባቸው!!!

Posted: 03 Sep 2021, 12:56
by Horus
የአማራ ክልል እጅግ ተደጋፊና ትክክለኛ እርምጃ እየወሰደ ነው ። ይህም የክልል ሰንደቁን ከድሮ ባተዋር፣ ባዕድ ቀለም ሰማያዊ ልዩ ያማራ መለያ ያለው እውነተኛው የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ እንዲሆን እየወሰነ ነው ። ይህ ትልቅ እርምጃ ነው ።

በእኔ ጽኑ እምነት በአስቸኳይ ሰንደቁን በአረንጓዴ ቢጫ ቀይ መለወጥ የሚገባው ጉራጌ ነው ። ለምሳሌ የጉራጌ ባህላዊ ልብስ ሆኖ ዲዛይን የሆነው ከአረንጓዴ፣ ቢጫ ቀይ ቀለሞች የተሰራ ጥልፍና ቅርጻ ቅርጽ ያለው ስለሆነ እጅግ ትክክል ነው። በዚሁ መሰረት የጉራጌ ልዩ ምልክት የሆነው ወይ ጎጆ፣ወይ እንሰት፣ ወይ ጣባ ምልክት ያለው የኢትዮጵያ ሰንደቅ (አረንጓዴ ቢጫ ቀይ) መሆን ግድ፣ ግድ ይለዋል ።

አቢይ ኢትዮጵያን አንድ ማድረግ ና ይህን የቀለሞች ቀውስ ማስወገድ ከፈለገ በፓርቲ ውሳኔ አድርጎ እያንዳንዱ ክልል ሆነ ጎሳ ባንዲራ የራሱ ልዩ ምልክት ያለበት የኢትዮጵያ ስንደቅ አላማ እንዲሆን መወሰን ይገባዋል ። ማለትም እነዚህ ክልልና ጎሳዎች ሁሉም ኢትዮጵያዊ ናቸው። አረንጓዴ ቢጫ ቀይ የሁሉም ቀለም ነው ። አንድ ጎሳ የራሱን የሚለየው ምልክት ካለው ያን ምልክት ከኢትዮጵያ ባንዲራ ላይ መጨመር ብቻ ነው ። ይህ ለሁሉም መደረግ አለበት ።