አቢይ አህመድና የትግሬ ጦርነት
Posted: 03 Sep 2021, 02:01
በመስከረም 24 2014 አቢይ አህመድ የምር የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ይሆናል ። ዛሬ ላይ ቆመን መላ ኢትዮጵያ መንግስት በትግሬ የሚያደርገውን ጦርነት ይደግፋል። ይህ ለምን ሆነ? ትግሬዎች ራሳቸው የፈጥሯቸው ክልልሎች በሙሉ ወታደር፣ ገንዘብ፣ ሰንጋ እና ሌላም ሌላም ድጋፍ ወደ ትግሬ ጦርነት እንዲልኩ የሚገፋቸው ፍላጎት ምንድን ነው?
ሁለት ነገሮችን ብቻ ጠቅሼ ላቁም። አንዱ የአቢይ አህመድ ወደፊት ዕድልና የጎሳ ፖለቲካ ስርዓት ነው። ሁለተኛው ጦርነቱና የትግሬ ወደፊት ዕድል ነው።
የጎሳ ፖለቲካ በዕድሜ 50 አመቱ ነው። በነዚህ 50 አመታት ውስጥ ይህ የዘር አይዲዮሎጂ መጓዝ የሚችለውን ርቀት ተጉዞ፣ መፍጠር የሚችለውን ችግርና ቀውስ ፈጥሮ እየሞተ ነው።
ትግሬ በሚመለክት ያለው ሃቅ ይህ ነው። የትግሬ ማህበረሰብ ፍጹም የተሳሳተ ሃዲድ ላይ ወጥቶ በሁሉም መልኩ መፍረስ የጀመረው ዛሬ ሳይሆን የዛሬ 50 አመት ነው። ይህ የጎሳ ክፍፍልና የዘር ፖለቲካ ሄዶ ሄዶ ማብቂያው ጦርነት፣ እልቂትና ራሱ የትግሬ ማህበረሰብ እንደ ማህበረሰብ መፍረስ እንደ ሚሆን ሺ ግዜ ተብሏል። ዛሬ የምናየው የትግሬ አጥፍቶ መጥፋት ማህበራዊ እብደት ለ50 አመታት ሲጠራቀም የመጣው የትግሬ ልሂቃን ታሪካዊ ስህተት ውጤት ነው። ትግሬ ከዚህ በራሱ ህሳቤና መለወጥ ከዚህ መቀመቅ ሊወጣ አይችልም ። የትግሬ መፍትሄ የሚመጣው ከኢትዮጵያ ነው።
አቢይ አመድ በሚመለከት ያለው ሃቅ ይህ ነው። አቢይ እንደ ነገ መስከረም 24 ለሚቀጥለው 6 አመት የኢትዮጵያ መሪ ይሆናል ። በኢትዮጵያ ውስጥዊ እድገት፣ በቀጠናውና አፍሪካ መገንባት ስላለባቸው ውህደቶች፣ ትብብሮች ላይ አቢይ ያለው ራዕይ የሚያከራክር አይደለም ። ምናልባት 90% የህዝብ ድጋፍ ይኖረዋል። የአቢይ አህመድ መሰረታዊ ችግሮች ያሜርካ እቀባና ግፊት አይሆኑም ። ነገር ግን አቢይ አንድና አንድ የማያልፈው ችግር አለበት ።
ይህም የጎሳ ስርዓት ነው። በኢትዮጵያ በዘር፣ በጎሳ፣ በክልል የተከፋፈለ የጥላቻ የጥርጣሬ የፉክክር፣ የፉክቻ የግጭት እና የቀውስ መንግስትና ስርዓት እየመራና በዚያ ላይ ቆሞ እንኳንስ አፍሪካና ቀጠናውን ማዋሃድ ቀርቶ የኢትዮጵያን ውስጣዊ ዶሜስቲክ አጀንዳ ተግባራዊ ሊያደርግ አይችልም ። የትግሬ ጦርነት ቢቆም እንኳ ሌላ የጎሳ ጦርነት ይፈነዳል ።
አቢይ አህመድ ታሪክ ግዙፍ እድል ሰጥቶታል ። ግን እሱም እንደ ትግሬዎቹ በጎሳ የጭለማ ፖለቲካ ተመላልሶ ታሪካዊ ዕድሉን አባክኖ እንደ ትግሬዎቹ ሊወድቅ ይችላል ። ይህ እንዳይሆን የሚመራው ብርሃን ካለና የዚህ የማይቀር ታሪካዊ ምጽአት ማስተዋል ከቻለ ስልጣን ከያዘ ማግስት ጀምሮ ኢትዮጵያን ከዚህ በስብሶ ከፈረስው የዘር አይዲዮሎጂና የጎሳ ሕገ መንግስት ማላቀቅ፤ አገሪቱን ሕዝቡን ከዚህ ተስፋ አልባ የመሃይሞች ህሳቤና የመከራ አይዲዮሎጂ ነጻ ማውጣት አለበት ።
የዘር ፖለቲካ እስካለ ድረስ አቢይ የወጣትነት ጉልበቱን በከንቱ አምክኖ የመልስና ሃይለማሪያም ጽዋ ይቀምሳል ። የዘር ፖለቲካን ከኢትዮጵያ ለማጥፋት ቆርጦ በድፍረት፣ በጽናት ከተነሳ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ታላቁ የአፍሪካ መሪ የመሆን ዕድል በእጁ ወስጥ አለው ።
በአንድ ቃል የትግሬ ጦርነት የሚነግረን ታሪካዊ ሃቅ የዘር ፖለቲካ መሞቱን፣ ያን ሃሳብ የሙጥኝ ያሉና የሚሉ ሁሉ መፍረሳቸውን ነው ። የዛሬ የትግሬ ጦርነትና አሳፋሪ እልቂት ዛሬ የመጣ ሳይህን የዛሬ 50 አመት ትግሬዎች ያወጁት የጎሳ ማኒፌስቶ ተቀጥያና መደምደሚያ ነው ።
ሆረስ ዐይነ ኩሉ