- "ስለ ሰላም ኣሁን ማውራት TPLFን መደገፍ፤ ከTPLF ጋር እንደመወገንና እንደ መሰለፍ ነው የሚቆጠረው።"
- "ሰላም የማይፈልግ የለም፤ ኣሁን የሚላያየን ሰላም የሚመጣበት መንገድ ነው። በነፍጥ ብቻ ብሎ የሚያስብ ሰው ኣለ፤ በነፍጥ ሰላም ማምጣት የሚቻል ቢሆን ኖሮ፤ ባለፉት 50 ዓመታት ኣንታመስም ነበር። ዘላቂ ሰላም የሚመጣው በመሸናነፍ ነው ብየ ኣላምንም። ዘላቂ ሰላም የሚመጣው ማንም የማይሸነፍበት ኣማራጭ ስናመጣ ነው። win-win የሚሉት ፈረንጆቹ ማለት ነው። እኔም ኣንተም ሳንጎዳ ነው ትክክለኛው ሰላም የሚመጣው። ኣንደኛው ተደፍጥጦ፤ ሌላኛው ደፍጥጦ በተኣምር ዘላቂ ሰላም ኣይመጣም።"
- "መጠፋፋት ቀላል ነው። ተጨማሪ ቂም፤ ተጨማሪ ቁርሾ፤ ተጨማሪ ጥላቻ፤ ልንጨምርበት ካልሆነ በስተቀር፤ ዘላቂ ሰላም ኣያመጣም።"