የጸጥታ ጥበቃው ምክር ቤት በትግራይ ጉዳይ ላይ ለ8ኛ ጊዜ ሊመክር ነው
Posted: 24 Aug 2021, 21:07
የጸጥታ ጥበቃው ምክር ቤት በትግራይ ጉዳይ ላይ ለ8ኛ ጊዜ ሊመክር ነው
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታ ጥበቃው ምክር ቤት፤ በኢትዮጵያ በትግራይ ክልል ባለው ነባራዊ ሁኔታ ላይ በመጪው ሐሙስ በዝግ ሊመክር ነው። ምክር ቤቱ በትግራይ ክልል ውጊያ ከተቀሰቀሰ ወዲህ በጉዳዩ ላይ ሲወያይ የሐሙሱ ለስምንተኛ ጊዜ ነው።
የትግራይ ሁኔታን በተመለከተ የጸጥታው ምክር ቤት ስብሰባ እንዲያደርግ የጠየቁት ስድስት ሀገራት መሆናቸውን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየርላንድ ተልዕኮ ከቀናት በፊት በትዊተር ገጹ ባወጣው መረጃ አስታውቆ ነበር። ይህን የስብሰባ ጥሪ ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ነሐሴ 13 በጋራ ያቀረቡት አየርላንድ፣ ኢስቶኒያ፣ ፈረንሳይ፣ ኖርዌይ፣ ብሪታኒያ እና አሜሪካ መሆናቸውን ተልዕኮው ጠቁሟል።
ስድስቱ ሀገራት ስብሰባው እንዲካሄድ የጠየቁት፤ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በኢትዮጵያ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ጥሪ ማቅረባቸውን ተከትሎ ነው። ጉተሬዝ በሐሙሱ ስብሰባ ላይ ተገኝተው በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቁ የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የዲፕሎማቲክ ምንጮች ተናግረዋል።
ከተመድ ዋና ጸሀፊ በተጨማሪ በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ በተጓዙበት ወቅት ትግራይን ጎብኝተው የተመለሱት የድርጅቱ የሰብዓዊ እና የአስቸኳይ እርዳታ አስተባባሪ ማርቲን ግሪፊትዝ በስብሰባው ላይ እንደሚሳተፉ እነኚሁ የዲፕሎማቲክ ምንጮች ገልጸዋል።
https://ethiopiainsider.com/2021/4348/