Page 1 of 1

የአፄ ዮሃንስ ልጅ የልዑል ራስ አርዓያ እና የአፄ ሚኒሊክ ልጅ የልዕልት ዘውዲቱ የጋብቻ ሽኝት ሥነ ሥርዓት

Posted: 24 Aug 2021, 09:34
by sarcasm
I love history and I thought I'd share with you the below account of the 19th century royal wedding.

የአፄ ዮሃንስ ልጅ የልዑል ራስ አርዓያ እና የአፄ ሚኒሊክ ልጅ የልዕልት ዘውዲቱ የጋብቻ ሽኝት ሥነ ሥርዓት።

(የልዕልት ዘውዲቱና የልዑል ራስ ሣህለ (አርዓያ)ሥላሴ ጋብቻ የሚካሄደው በሃይማኖታዊ ስነ ሥርዓት ነው። ይሁን እንጂ እድሜያቸው ገና የ7 እና 12 አመት ልጆች በመሆናቸው የትዳር ህይወታቸውን የሚጀምሩት ከአመታት በኋላ ይሆናል።)



ከዛሬ 138 ዓመት በፊት በጥቅምት ወር 1875 ዓ.ም ፈረንሳዩ ሚስተር ሶለዬ ለንግድ ስራ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ ተጉዞ በነበረበት ጊዜ ሸዋ ላይ በዚያ ጊዜ የሸዋ ንጉሥ ከነበሩት ከንጉሥ ሚኒሊክ ጋር ተገናኝቶ ነበር። በዚህ አጋጣሚም የ 12 ዓመቱን የአፄ ዮሃንስ ልጅን የልዑል ራስ ሣህለ (አርዓያ) ሥላሴን እና የ7 ዓመቷን የንጉሥ ሚኒሊክ ልጅን የልዕልት ዘውዲቱን የጋብቻ የሽኝት ሥነ ሥርዓት ላይ የመገኘትና የመዘገብ እድል አግኝቶ ነበር።እኔም ባለኝ ትንሽ የፈረንሳይኛ ችሎታ ፈረንሳዊው ሚስተር ሶለዬ የጉዞዬ ማስታወሻ ብሎ ካሳተመው OBOK-LE CHOA-LE KAFFA ከሚለው መፅሃፍ ላይ ይህንን ክፍል ባጭሩ ተርጉሜ ለአንባቢዎች አቅርቤዋለሁ።

"ጥቅምት 9 ቀን 1875ዓ.ም ፦ በጠዋት የንጉሡን ከቤተ መንግስት መውጣት የሚያበስረውን የጥሩንባ እና የነጋሪት ድምፅ ሰማን ። እንደተነገረንና እንደተረዳነው ንጉሥ ሚኒሊክ የልጃቸውን ጋብቻ ምክያት በማድረግ ከጦር አለቆቻቸው አንዱ ከሆኑት ከራስ ጎበና የተላከላቸውን ስጦታ አካባቢው ከሚገኘው ሰፊ ሜዳ ላይ ለመቀበል ነው።

እኛም ፈረሶቻችንን ጭነን ግማሽ ሰዓት ያህል ከተጓዝን በኋላ ቀጠሮው ቦታ ደረስን ቦታውም ትልቅ ሰፊ ሜዳ ሲሆን በቁጥቋጦ የተከፈለና አንዳንድ አጫጭር ዛፎች ያሉበት ቦታ ነው።

ንጉሡ አንድ ከሚያምር አመድማ በቅሎ ላይ የተቀመጡ ሲሆን የበቅሎው ኮርቻ በአረንጓዴ ሃር የተሰራና ዘርፈ ወርቅ ነው ። በአንድ ባለባበሱ ያማረ የጦር አዛዥም ታጅበዋል።

ስጦታውን የሚያቀርበው የራስ ጎበና ልጅ ባል ሲሆን ስጦታውም 1300 ፈረስ ከዚህ ውስጥ 500 ባለኮርቻ ሲሆን 300 መቶ ደግሞ በብር ያጌጡ ናቸው።እንዲሁም 300 መቶ በቅሎ ከዚህም ውስጥ 100 ከኮርቻ ጋር ሲሆን ወርቅ፥ የዝሆን ጥርስ እና ከጥርኝ የሚገኘውንና ለሽቶ ስራ የሚያገለግለውን ፈሳሽ ነው።

ቀኑ በጣም ደስ የሚል ሲሆን በፀሃይ የሚያብረቀርቀው የፈረሶች ኮርቻና ባማረው ነጭና ቀይ በለበሱት ሰዎች ልብስ ለዓይን ልዩ ድምቀት ሰጥቶት ነበር።
ጥቅምት 10 ፦ የኔ ጓደኛ የሆነው አቶ ሊዮ የፎቶግራፍ ማንሻ ስለነበረው የሚታይ ነገር ፍለጋ በማለት በማለዳ ወጣን ነዋሪዎቹም እኛን ለማየት በሚያደርጉት ግርግር አንዳንድ አስቂኝ ነገሮች ጠፈጠሩ።

ጥቅምት 11 ፦ ንጉሠ ነገሥት አፄ ዮሃንስ የልጃቸውን እጮኛ ለመውሰድ ከመንግሥታቸው ሶስት ራሶችን ጨምሮ ታላላቅ ሰዎችን ከአንድ ሺህ ስምንት መቶ ወይም ሁለት ሺህ ከሚሆኑ አጃቢዎች ጋር ወደ ንጉሥ ሚኒሊክ በመላካቸው ንጉሡም ዛሬ እነዚህን ሰዎች በክብር ይቀበሏቸዋል።

እኛም የእግር መንገዳችንን ካለንበት ሶስት ወይም አራት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ወደ ሰፈሩት የአጼ ዮሃንስ ሰዎች ጋ አደረግን።ይሁን እንጂ ክብርን በሚነካ ሁኔታ ነው የተቀበሉን በግልፅ ለመናገር ሊያስጠጉንም አልፈለጉም የፎቶግራፍ ማንሻችንም እንደ መተተኛ እና ክፉ ነገር እንደምናመጣ ነው ያስቆጠረን።ወደ አራት ሰዓት ግድም እንደተመለስን የንጉሱ ሠራዊት መሳሪያ ታጥቆና ተሰልፎ አገኝነው።

በ 5 ሰዓት የትግራይ ሰዎች በሰልፍ ሆነው ደረሱ ከፊት የተመረጡ ተኳሾች በብር በተጌጡ ፈረሶች ላይ ሆነው ተሰልፈዋል ጸጉራቸውን በክብ የተሰሩና ያንበሳ ጎፈር ያጠለቁ ናቸው።ከበፊተኛው ረድፍ ቀጥሎ ያሉት የተወሰነ ቁጥር ያላቸው የተማረኩ የቀድሞ የግብጽ ወታደር የነበሩ አሁን አጼ ዮሃንስን በማገልገል ላይ ያሉ የሱዳን ወታደሮች ናቸው።

ከዚህ ቀጥሎ ሶስት ራሶች በነጭ በቅሎዎች ላይ ተቀምጠው ይከተላሉ በእድሜው ከፍ ያለውና በመሃል የተቀመጠው ጸጉሩን በክብ ጉንጉን ተሰርቶታል።

ከራሶቹ ቀጥሎ በበቅሎ የተቀመጡ የተከበሩ ሰዎች በደማቅ ሰልፍ ይከተላሉ ከነሱ ጀርባ ብዙ ሰዎች በእግራቸው እየተከተሉ ይዘፍናሉ ጠመንጃቸውንም ወደ ላይ እያነሱ ይፎክራሉ።ራሶቹም ቀድመው ወደፊት ሲያልፉ በሰልፍ ሆኖ የሚጠባበቀው የንጉሡ ሠራዊት ሶስት ጊዜ እስከመሬት ዝቅ ብሎ እጅ በመንሳት ሰላምታ አቀረበላቸው።

ጥቅምት 12 ፦ የቤተ መንግሥቱ እና የከተማው ዋና ስራ የንጉሡን ስጦታ ከራሶቹ ጋር ለመጡት እንግዶች ማዳረስ ነበር ስጦታውም ፈረስ፥ በቅሎ ፥ጠመንጃ ፥ ልብስና ገንዘብ ነበር።በዚህም ስጦታ ተደስተው የትግራይ ሰዎች እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ ሲጫወቱ አመሹ ።

ጥቅምት 13 ፦ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ንጉሥ ሚኒሊክ ልጃቸውን ልዕልት ዘውዲቱን የሚሸኙበት ቀን ነው። ከትግራይ የመጡት ራሶች አጼ ዮሃንስ እና የወደፊት ትዳር አጋሯ የሚሆነው ልጃቸው ልዑል ራስ ሣህለ(አርዓያ) ሥላሴ ወደሚጠብቋት ቦታ ወደ ቦሩ ሜዳ ይዘዋት ይሄዳሉ።

ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት ጀምሮ ሁሉም የሸዋ ሠራዊት እንደትናንቱ የጦር መሳሪያውን ይዞ ተሰልፏል ። ሁሉም ሰው በወርቃማና ብራማ ቀለም ያጌጠ የበዓል ልብስ ለብሰዋል።እኛም ከቤተ መንግሥቱ መውጫ በር በታች በኩል እንጠብቃለን። አጠገባችን ያለች አንዲት ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ውድ የተክህኖ ልብስ ለብሰው ሥነ ሥርዓቱን ለመባረክ ወጥተዋል የቆዳ ልብስ የለበሱ መነኩሴዎችም አብረው ተቀላቅለዋል።

እኔ የምገኘው ሚስተር አልፈሪ ካስተዋወቀኝ አርመናዊ ከሆነው ከዶክተር ጎርጉሃስ አጠገብ ነው።አቶ ጎርጉሃስ የተወለደው ቁንስጥንጥኒያ ሲሆን በካይሮ የከረጅም የሙዚቃ መምህርነት በኋላ በትግራይ በኩል እዚህ መጥቶ ለንጉሡ የንግድ፥የጥበብ ውጤቶችንና ፥ የልብስ ስፌት ስራዎችን ይሰራል በተለይም በሃር ጨርቅ በሚሰራቸው ባርኔጣዎች ታዋቂነትን አትርፏል።

በ5 ሰዓት 50 ላይ የሽኝቱ ሥነ ስርዓት ከቤተ መንግሥቱ ተጀመረ በሰልፍ የሚጠብቁት ወታደሮችም ወደ ሰማይ በመተኮስ ሰላምታ አቅርበው ጠመንጃቸውን አፈሙዙን ዘቅዝቀው ትከሻቸው ላይ አሳረፉ ይህም ልዕልቲቱ ተለይታ የመሄዷን ሃዘን ለማሳየት ነው።

የሽኝቱ ሰልፍ በእውነት በጣም ግዙፍ የደመቀና ልዩ ነው የቤዛንታይንን ስርወ መንግሥት የበአል አከባበር ሥርዓትን የሚያስታውስ ነው። ከፊለፊት መጫኛቸው በውድ ያጌጡ 20 በቅሎዎች እያንዳንዳቸው ጨርቅ የለበሱ ሁለት ሁለት ነጋሪት ተጭነዋል።ኢትዮጵያ ውስጥ ነጋሪት የሃይል ማሳያ ምልክት ሲሆን በጦርነት ጊዜ ነጋሪት መያዝ ልክ በአውሮፓውያን ዘንድ ባንዲራ እንደመያዝ ይቆጠራል። ቀጥሎ የመጡት ቆዳ እና ቢጫ ልብስ የለበሱ ካህናት ሲሆኑ ሁሉም የካህናት ምልክት የሆነውን ነጭ ጥምጥም ጠምጥመዋል።

ከዚህ ቀጥሎ የመጡት ደግሞ ማንኛውም የህብረተሰቡ ክፍል ሲሆን ግማሹ በእግር፥በፈረስና በበቅሎ ናቸው። ትልልቆቹ መኳንንት የተለያዩ ቀለም ያላቸው ጃንጥላዎች ተይዞላቸዋል ወታደሮችም ደስ በሚል ዜማ እየዘፈኑ ይጨፍራሉ እንደተረጎሙልኝ በእውነት ወኔ የሚቀሰቅስ ነው።

ልዕልቲቷን በዙሪያዋ የከበቧት አገልጋዮች ወይም እመቤቶች በጨርቅ በተጌጡ በቅሎዎች ላይ ተቀምጠዋል እያንዳንዳቸው እግራቸው ድረስ የሚጎተት ቀሚስ ለብሰዋል። ሁለት ወይም ሶስት መቶ የሚገመቱት ሁሉም አጃቢ ሴቶች ውድ ልብስ ለብሰዋል እያንዳንዳቸውም የሙሽራዋን ቅርጫት ይዘዋል።በዚህ ጊዜ ነው የልብስና የጌጣጌጥ አይነት ሰልፍ ያየነው።

ከነሱ በኋላ ያሉ ሙዚቀኞች ዋሽንትና ጥሩንባ ይዘው ይጫወታሉ። አንድ ሴት የልዕልቲቱን የጸሎት መጽሃፍት በተለያየ ቀለም ባላቸው ክሮች በተሰሩ ቦርሳዎች አንግታ ይዛለች።

ከዚህ ቀጥሎ ሁለት ፊታቸው የተሸፈነ ወጣት ሴቶች ያማረ ወርቃማ ሃር ልብስ ለብሰው ባጌጡ በቅሎዎች ላይ ተቀምጠዋል።አለባበሳቸው ተመሳሳይ ሲሆን የበቅሎ ያዥያቸው ቁጥርም ተመሳሳይ ነው።አንደኛዋ ሶስት ጥላ የተያዘላት ሲሆን ሁለተኛዋ ግን ምንም አልተያዘላትም። እሷም የንጉሡ ማደጎ ልጅ እና የልዕልቲቱ አብሮ አደግ ስትሆን ከልዕልቲቱ የሚለያት ነገር ቢኖር ይኸው ጥላ ለሷ ያለመያዙ ብቻ ነው።
ሌላው ልብ የሚነካው ነገር የሰዎች ሁሉ እኩልነት ነው ታላላቆቹ ሰዎች ሁሉ ወደ አደባባይ ሲወጡ አጅቧቸው እንደሚወጣው እንደማንኛውም ተራ ሰው ነው እኩል ለብሰው የሚታዩት።ንጉሠ ነገሥቱም ቢሆን ልክ እንደ አንዱ መኮንን እንደ ሊቀ መኳሱ ነው ለብሶ የሚታየው።

በበቅሎ ላይ የተቀመጠች አንዲት ልጃገረድ የልዕልቲቱን ቀይ ቀለም ያለውና ጠርዙ በወርቅ ጌጥ የተጌጠውን ጫማ በጀርባዋ አዝላ ትከተላታለች። በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኬደው በባዶ እግር ወይም በሰንደል ጫማ ነው ሽፍን ጫማ ነንጉሣውያን ቤተሰቦችና ለቤተክርስቲያን አለቆች ብቻ የተወሰነ ነው። በዚህ የተነሳ ትላልቅ ሰዎች ደረጃቸውን ለማሳየት ሲሉ ይጫሙታል።
ሰልፉ ከትግራይ በመጡት ራሶችና አጃቢዎቻቸው ተጋርዷል ማለት ይቻላል ትንሿ ንግሥት በአጠገባችን ስታልፍ ካህናቱ በከበሮና በጽናጽል ዳዊት በታቦተ ጽዮን ፊት እንዳሸበሽበው እያሸበሸቡና እየዘመሩ የሰማያዊውን ምርቃት ሁሉ አወረዱላት።

ከዚያም ቀጥሎ በጀርባቸው ጠጅና ጠላ የተሞላ እንስራ ያነገቱ ሴቶችና እንዲሁም የወጥ ቤት ሰራተኞች የምግብ መስሪያ እቃዎቻቸውን በብዛት በበቅሎና በአህያ ጭነው ይከተላሉ።ፈታዮችም በአህያና በበቅሎ ከተጫነ ጥጥ ጋር አብረው ይጓዛሉ። ጠቅላላ የሚጓዘው ጭነት ሁለት መቶ በቅሎና አህያ ይሆናል።ለሥጋ የሚሆን ከፍተኛ ቁጥር ያለው ከብትም አብሮ ይጓዛል።

ወጣቷ ልዕልትም በዛሬው ምሽት በትግራይ ሰዎች ሰፈር አድራ ነገ በጥዋት የጋብቻው ስነ ሥርዓት ወደሚካሄድበት ወደ ቦሩ ሜዳ ትጓዛለች።

የልዕልት ዘውዲቱና የልዑል ራስ ሣህለ (አርዓያ)ሥላሴ ጋብቻ የሚካሄደው በሃይማኖታዊ ስነ ሥርዓት ነው። ይሁን እንጂ እድሜያቸው ገና የ7 እና 12 አመት ልጆች በመሆናቸው የትዳር ህይወታቸውን የሚጀምሩት ከአመታት በኋላ ይሆናል።"

ከታሪክ እንደምንረዳው አፄ ዮሃንስም ሆኑ አፄ ሚኒሊክ ለአገራቸው ኢትዮጵያ ነፃነት አንድነትና እድገት ይጥሩ የነበሩና በትግራይ እና በአማራ ነገሥታት መካካል ይነሳ የነበረውን የሥልጣን ሽኩቻ በጋብቻ በማስተሳሰር የአማራን እና የትግራይን ማህበረሰብ አንድ ለማድረግ ጥረት ማድረጋቸውን ይህ ጽሁፍ በግልጽ ያስረዳናል።ይሁን እንጂ አለመታደል ሆነና ልዑል ራስ ሣህለ (አርዓያ)ሥላሴ በወጣትነት ዘመኑ ከልዕልት ዘውዲቱ ልጅ ሳያፈራ 21 ዓመቱ በሞት በመለየቱ ልዕልት ዘውዲቱም ወደ ቤተሰቦቿ ተመልሳለች።ከዚህም ጋብቻ የሚወለደው ህፃን ዙፋኑን ወርሶ ሁለቱንም ማህበረሰቦች አንድ አድርጎ ይገዛል የሚለው ሀሳብም ሳይሳካ ቀርቷል።

ጌቱ ከፈረንሳይ

https://www.facebook.com/getu.seleshi/p ... 7570339349

Re: የአፄ ዮሃንስ ልጅ የልዑል ራስ አርዓያ እና የአፄ ሚኒሊክ ልጅ የልዕልት ዘውዲቱ የጋብቻ ሽኝት ሥነ ሥርዓት

Posted: 24 Aug 2021, 15:43
by Abere
Thanks for sharing. This story is very interesting despite the sad ending of the lives of both the princes and the princess. I wish the couples survived by children born out of their marriage bond. What is more interesting above all, people of that time were light years a head of the generation of this time. Regardless of their nobility and rank, leaders in the good old time were genuinely working for social cohesion through various available means. They used to have wives or concubines from most tribes or religious groups. For instance, Liji Iyasu had many children from different wives; and Emperor Tewodros is believed to have children from several women as well. It appears they had a far advanced out look compared to today's so called PhD or degree holders. It is a recent memory that Dr. Merara Gudina, Bekele Geriba, etc. were denouncing inter ethic marriages; and also Alula Solomon was instructing those Tigres married to Amhara get divorced as well as those in love to break away. How would those of our ancestors in that good old time say when hearing Tigre husbands and wives in Gondar Ma-Kadra massacred their Amhara spouses? Very shocking and indeed sad. The cause of all this is TPLF - in stead of cultivating love and harmony it worked so hard seeding hatred , division and genocide. And the result, we all are harvesting it now. More upsetting, the enabling support provided by most Tigres to TPLF to continue such ugly practice.

Re: የአፄ ዮሃንስ ልጅ የልዑል ራስ አርዓያ እና የአፄ ሚኒሊክ ልጅ የልዕልት ዘውዲቱ የጋብቻ ሽኝት ሥነ ሥርዓት

Posted: 24 Aug 2021, 16:35
by Thomas H
This story looks like my story. My fiancée is a Gojame and I am a Tigrayan. I Hope Halafi Mengedi will agree to be a Godfather of our mixed Tigrayan-Gojame child.

Re: የአፄ ዮሃንስ ልጅ የልዑል ራስ አርዓያ እና የአፄ ሚኒሊክ ልጅ የልዕልት ዘውዲቱ የጋብቻ ሽኝት ሥነ ሥርዓት

Posted: 24 Aug 2021, 19:36
by sarcasm
Abere wrote:
24 Aug 2021, 15:43
What is more interesting above all, people of that time were light years a head of the generation of this time. Regardless of their nobility and rank, leaders in the good old time were genuinely working for social cohesion through various available means.
The leaders in those days have always went for win-win solutions by marrying their children to the children of the other leaders who they fought against to get the nuguse negest title. In that way they are giving their opponents the opportunity of having their children or grand children of becoming kings or better nuguse negest. So even if they'd lost the battle for nuguse negestnet at that time, they would be comforted by the knowledge that their offsprings have been afforded a better chance.