Page 1 of 1

አንድ የባንዳ ጄ/ል ማአሾ በየነ በእጀ ሙቅ ታበተ!!

Posted: 20 Aug 2021, 22:44
by Horus
ሆረስ ነኝ፣ አንድ ታሪክ ጀባ ልበላችሁ።

ድሮ በኢትዮጵያ ቋሚ የፖሊስ ጣቢያና እስር ቤት በአልነበረበት ዘመን፣ አንድ ሰው በሌላ ሰው ላይ ወንጀር ከፈጸመ የንብረት እዳ ካለበት ከሳሹ ተከሳሹን በሕግ አምላክ አስገድዶ ወደ ዳኛ ፊት ያመጣው ነበር። ተከሳሹም ካሳ እንዲከፍል ቅጣት ተበይኖበት ሶስት ምርጫዎች ይሰጡት ነበር። መቀጮውን ከፍሎ በነጻ ወደ ቤቱ መሄድ፤ ይህን ማድረግ ካልቻለ ከከሳሹ ጋር በሙቅ ይታበት ነበር ። ማበት፣ አበተ ማለት አሰረ፣ ተበተበ ማለት ነው ። ተከሳሽ እዳውን እስከ ሚከፍል ድረስ ካሸናፊው ይታበት ነበር። ተቀጪው ዋስ የሚሆነው ሌላ ሰው ካገኘ ያ ዋስ በምትኩ ከባለንብረቱ ጋር ይታበት ነበር ።

ዛሬ ከዚያ ታሪክና የሕግ ባህል በመጣ ነው ዋስ ወይም የተውሶ እስረኛ የሚለው ግዙፍ የሕግ ቃልና ጽንሰ ነገር የተሰየመው ። ዋስ ማለት የተውሶ ምትክ ማለት ነው ። ይልቅስ ትልቁ ቃል መብት የሚለው ነው ። በሕግ ሳይንስ ውስጥ መብት (ራይት) የሚባለውን ጽንሰ ነገር የሚበልጥ ቃል የለም ። ይህ መብት የሚባለው የሕግ ክንሴፕት አበተ፣ አሰረ ከሚለው በሙቅ መታበት የመጣ ነው ። የመብት እና ዋስ ስረቃል እና ታሪካዊ አመጣጥ እንዲህ ነበር ።

ይህን ጉዳይ ያስታወሰኝ አገር የከዳው ባንዳ ጄ/ል ማአሾ በየነ ሁለት እጆቹ በብረት ሙቅ ታብቶ ሳይ ነው :lol: :lol: