Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42779
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ድፊት

Post by Horus » 18 Aug 2021, 14:11

(ድጋሚ ፖስት፤ የዛሬ ወር አካባቢ ስለሰራዊቱ ወደ አማራ ድንበር ማፈግፈግ የድፊት ስልት ነው ብዬ ነበር)

ድፊት የቆቅ ማደኛ ብልሃት ነው። ልጆች ሆነን ቆቅ የምናድነው በድፊት ነበር። ቆቅ እንደ ሚታወቀው በጣም ጥንቁቅ ወፍ ነች፣ በቀላሉ ለመያ ታስቸግራለች ። ታዲያ የኛ ብልሃት (መች እንደ ተጀመረ ባላቅም) ድፊት መስራት ነበር ። የቃሉ ውስጠ ትርጉም ወጥመድ ማለት ነው ። ድፊት አንድ ትልቅ ሳጤራ ወይም ትንሽ የቤት ክዳን ይመስላል። ከሸንበቆ እና ልጣጭ ነው የምንሰራው ። ከላይ ለጅ ማስገቢያ ቀዳዳ መስኮት እያበጅለታለን ።

ታዲያ ቆቆች በሚደበቁበት ጫካም ሆነ ቁጥቋጦ ወስጥ ይህን ቅርጫት ወስደን ባንድ በኩል ከፍ አደገን ከስር ከፈት በማድረግ በትንሽ ባላ እንደግፈዋለን፣ በባለው ወደ ላይ በመያዝ ማለት ነው ። በባላው ትክክል በድፊቱ ወስጥ ነጫጭ ቦቆሎ ፍሬዎች እንበትናለን፣ ቆቆቹን ለማማለል ማለት ነው ። ይህን አድረገን ወደ ከብት ጥበቃና ጨዋታችን እንሄዳለን።

አሁን ቆቆች ልክ እንደ ዶሮ ጥሬያቸውን ለመጫር ዘው ቱር ሲሉ ያን ያማረ ቦቆሎ ያያሉ። እየተንደረደሩ ለቦቆሎው ፍሬ ሲሽቀዳደሙ ከፍ
አድርገን በከፈትንላቸው ክፍተት ሲገቡ ባላውን አብሮ የጥሉታል። በዚያን ቅጽበት ድፊቱ መሬት ላይ ይደፋል ። ቆቆቹም ቦቆሎውን ለቅመው ከጨረሱ በኋላ ከባላው መውጣት አቅቷቸው እኛ በግዜያችን መጥተን ከላይ በሰራነው ትንሽ ቀዳዳ እጃችን አስገብተን ቆቋን ይዘን ከከብቶቻን ጋር ሲመሽ ወደ ቤት እንሄድ ነበር!

የቆቅ ስጋ በጣም ጣፋጭ ዶርን በእጅጉ የሚበልጥ ነው ።

ይህን የልጅነት ትዝታ ያመጣሁት የኢትዮጵያ ሰራዊት የዉጊያ ስልት ወይም ታክቲክ ቆቅን በድፊት የማደን ሜታፎርና ምስል ስለሆብኝ ነው ። እኒያ የጎንደርና የወሎ መሬቶች ነጫጩ ቦቆሎ ፍሬዎች ተመሰሉኝ። የትግሬ ባንዳዎች ይህን ቦቆሎ እያዩ ሰተት ብለው ድፊት ውስጥ ይገባሉ። ከዚያም ድሮን እያመለከተች ወታደርና ሄሊኮፕተር ይደበድባቸዋል!!

ለነገሩ ቆቅ ማሰብ ስለማትችል ነው የኛን የድፊት ብልሃት ማየት የማትችል! የትግሬ ባንዳ ምነው አርፎ እዚያ እትግሬ ምድር ቢኖር ዘሎ ድፊት ከሚገባ ብዬ ነው !!