Page 1 of 1

"ሰርጎ ገብ፣ ፀጉረ ልውጥ፣ ወይንም ጁንታ ስለሆነ ሳይሆን ትግሬ ስለሆነ ነው መጫወቻ የሆነው። ለሚያልፍ መንግስት የማያልፍ ዝምድናን አታላላ።"

Posted: 16 Aug 2021, 18:21
by sarcasm
ኧረ አንታወር ወገን

እዚ ሸገር ላይ የትግሬ አፈሳና እስር፣ ትግሬን ማንገላታት፣ የትግሬን ሱቅ መዝጋት፣ ማፈናቀል ኖርማል ሆኗል። ወላጆቹ ትግሬ የሆኑ፣ ወይንም ከወላጆቹ አንዱ የትግራይ ዝርያ ያለው፣ ራሱ ሙሉ ለሙሉ ትግሬ ሆኖ በትግሬነት ቀኖናና ዶግማ ያደገ የሸገር ኗሪ በሙሉ ራሱን ለአፈሳ፣ ለእስር እና ለመፈናቀል አዘጋጅቷል።
¤
ሰርጎ ገብ፣ ፀጉረ ልውጥ፣ ወይንም ጁንታ ስለሆነ ሳይሆን ትግሬ ስለሆነ ነው መጫወቻ የሆነው።
¤
ቲቪ ከፍተህ ፕሮፓጋንዳ ከሰማህማ፣ የሩዋንዳው ጭፍጨፋ ሁለት ወር ሲቀረው ከነበረው Mode ጋራ አይለይም። ከጎረቤትህ፣ ከጓደኛህ፣ ከአብሮ አደግህ ትግራዋይ ወንድምህ - አካባቢህን በንቃት ጠብቅ ይሉሃል። ትግሬው ጓደኛዬ ተጠርጥሮ እኔ ታምኜ መሆኑ እኮ ነው ፈሊጡ። . . . በስመአብ!
(ፍረድ)

እኔ በማውቀው ጦርነቱ ከጀመረ ጀምሮ #አንድም ትግሬ መሃል አገር ላይ ቦምብ አላፈነዳም። ሰው አልፈጀም። ተቋም አላነደደም። ባንክ አልዘረፈም። ተጠቁመው ቤታቸው ተፈትሾም፣ አብዛኞቹ ከህጋዊ ሽጉጥ ያለፈ እዚህ ግባ የሚባል መሳሪያ አልተያዘባቸውም።
¤
(እና ምን አርጉ ነው ሚባሉት?!)
¤
ገና ለገና ህወሃትን በልባችሁ ትወድዳላችሁ ተብሎ አፈሳና እስር አለ ወይ? ኦነግን የማይወድድ ኦሮሞ የለም እኮ።
¤
(ስማኝ አዲሳባ)
¤
ዛሬ ትግሬ ወዳጅህን አስጠላይ፣ ተከላካይ፣ አለሁልህ ባይ፣ ፖሊስና ካድሬ ጠቋሚ ቢመጣ በደቦ እምቢኝ ባይ ነው መሆን ያለብህ። ይህቺ ክፉ ቀን፣ ይቺ እኩይ ወርና አመት ታልፋለች። አቀያይማን ሳይሆን አዋድዳን ነው ማለፍ ያለባት። ነቃ ብለህ ከትግሬ አብሮ አደጎችህና ወዳጆችህ ጎን ሁን።
¤
➙ለሚያልፍ ቀን የማያልፍ ዝምታ ነውር ነው።
➙አለሁልህ፣ እኔ ቤት ና፣ ምን ልርዳ ይባላል።

➙ለሚያልፍ መንግስት የማያልፍ ዝምድናን አታላላ።
➙ከመንግስት እስር የኛ ዝምታ ይበልጥ ግፍ ነው።
➙ Integrity ያለውን ሰው ፕሮፓጋንዳ አይሸውደውም።
➙ ላሽ ላሽ በኔና በአንተ አያምርም።
Please wait, video is loading...