የትግራይ መንግስትም ሆነ ሰራዊት በኣማራ በኣፋርና በሌሎችም ክልሎችና ኣካባቢዎች በሚያደርጏቸው እንቅስቃሴዎች ከዞን በታች ያሉ ኣስተዳደሮች ስራዎቻቸውን መቀጠል እንዳለባቸው ያምናሉ:: በወንጀል ድርጊት ላይ በቀጥታ ከተሳተፋት ውጪ ሌላው ሁሉ በስራው እንዲቀጥል የየኣካባቢው ህዝብ የሚያቀርበው ጥያቄ ነው:: ስለዚህ ሁሉም ኣካባቢዎች ይህንን ልብ ሊሉ ይገባል:: ደጋግመን እንዳልነው ጠባችን ከህዝብ ጋር ሳይሆን ከሽፍቶች ጋር ነው::
ትግራይ ትስዕር!
Please wait, video is loading...