ሀገራዊ ጥሪ ወይስ ስልጣንን የማዳን ጥሪ?
Posted: 15 Aug 2021, 19:17
ሀገራዊ ጥሪ ወይስ ስልጣንን የማዳን ጥሪ ?

.
ሰሞኑን የብልጽግና ባለስልጣናት "ሀገርን የማዳን ጥሪ" በማለት ወጣቱን ለጦርነት እየጠሩት ናቸው። በትግራይ እና በኦሮሞ ህዝብ ላይ በግልፅ የጦርነት ክተት አውጀዋል። ልክ ሀገር በጠላት ወይም በውጭ ወራሪ ሀይል የተደፈረች ይመስል አፋቸውን ሞልተው "የሀገር ህልውና ዘመቻ" በማለት ጉዳዩን እያቀጣጠሉት ይገኛሉ።
.
እነዚህ የብልጽግና ሹማምንቶች ስልጣናቸው አደጋ ውስጥ ስለገባ የጭንቅ ጩኸት ላይ ናቸው። በሀገር ስም ወጣቱ በጦርነት ተማግዶ ስልጣናቸውን እንዲያተርፍላቸው እየተማፀኑ ነው። የሱዳንን የመሬት ወረራን "የህልውና ወይም ሀገርን የማዳን ጥሪ" በማለት ክተት አላወጁም። ምክንያቱ ግልፅ ነው - ሱዳን ለመሬት እንጂ ለእነሱ ስልጣን ስጋት ስላልሆነች ነው። ጉዳዩ ስልጣንን የማዳን እንጂ የሀገር የማዳን ጉዳይ አይደለም።
.
የትግራይ ህዝብን በኤርትራ እና በሶማሊያ ወታደሮች ብሎም በዱባይ ድሮኖች ጨፍጭፈው፣ የትግራይ ሉአላዊ መሬት የሆነውን ዘርፈው፣ አዘርፈው፣ ንፁሃንን ገድለው፣ ሴቶችን ደፍረው፣ ህፃናትን በረሃብ ቀጥተው፣ መሰረታዊ ልማቶችን እና ኢንዱስትሪዎችን አውድመው ሲያበቁ በእርግጥም እንዳሸነፉ ገምተው ነበር። ድሉ በእነሱ እጅ የሆነ የመሰላቸው ጊዜ ወጥተው ፎክረዋል፣ ሸልለዋል። "የህግ ማስከበር ዘመቻው ግቡን እስኪመታ እረፍት የለንም" ብለው ተናግረዋል። የትኛውንም አይነት ድርድር ሆነ ማባበያዎች እንደማይቀበሉ ገልፀው ነበር። አሁን ላይ ግን አሸናፊ ነኝ ብሎ ያሰበው ብልፅግና ተሸናፊ ሆኗል። አሳዳጅ የነበረው ተሳዳጅ ሆኗል። እየፎከረ የነበረው አሁን ላይ በእርግጥም እያለቀሰ ነው። ያልተገደበ የስልጣን ጥማቸውን ለማርካት የሀገር ደጀን የነበረውን የመከላከያ ሰራዊትን በጦርነት ማግደዋል።
.
በአሁኑ ግዜ የብልፅግና ሰራዊት እና ፎጤ አፈሙዝ ቁልቁል ደፍተው ወደ ቤታቸው እየተመሙ እና ከጦር ሜዳ እየሸሹ ባሉበት ወቅት ቄሶች ታቦት ይዘው በመውጣት የሚሸሹትን ወታደሮች እንዳይሸሹ ለመማፀን ብሎም ለመገዘት ማሰባቸው እየተነገረ ነው። ቀሳውስቱ ''ወደ ኋላ የሚሸሸውን ወታደር ገዝተናል፤ ጥቁር ውሻም ይውለድ ብለንናል'' እንደሚሉ ይጠበቃል። ቀሳውስቱ እንደተባለው የሚሸሽውን ወታደር የሚገዝቱ ከሆነ በሚቀጥሉት አመታት የሚወለዱ የጥቁር ውሾችን ብዛት እግዜር ያሳያቹ።
.
ወጣት ሆይ ንቃ! የማንን ስልጣን ለማዳን ነው የምትማገደው? የማንን ተስፋፊ ባለርስት መሬት ለመጠበቅ ነው ህይወትህን የምትከፍለው? የትኛውም የውጭ ወራሪ ለመመከት ነው ነብስህን አሳልፈህ የምትሰጠው? ጉዳዩ የሀገር ህልውና ሳይሆን የስልጣን ህልውና ነው።
.
ፊንፊኔ ታይምስ

Please wait, video is loading...