Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

"የግፋ በለው እብደት ለ50 ዓመት ሄደንበታል፤ ኣልሰራም። ንግግር በዶላር ኣይገዛምና በጠረጴዛ እንቀመጥ ርካሽ ስለሆነ። ለሰላም ዕድል እንስጥ። ጦርነቱ ማንም ኣይወስድብንም፤ ነገም የኛ ነው"

Post by sarcasm » 14 Aug 2021, 14:18

"አሁን ከዲሞክራሲ ጥያቄ ኣልፈን ወደ ህልውና ጥያቄ ውስጥ የተዘፈቅነው፤ እሱንም ደግሞ ማስቀጠል ያልቻለው ለምንድነው ሲባል፤ ይሄ ለ50 ዓመት የሄደው የግፋ በለው እብደት ነው። ሰው የራሱን ቤት እያቃጠለ፤ የራሱን ወንድሞች እየገደለ፤ ኣገር እያወደመ ኣሸናፊ ነኝ የሚልበት ኣካሄድ ነው። 50 ዓመት ሄደንበታል፤ ኣልሰራም። እስቲ ቢያንስ፤ ንግግር በዶላር ኣይገዛምና እንደ ጥይትና እንደ ቦንብ፤ በጠረጴዛ ዙርያ እንቀመጥ። ቢያንስ ርካሽ ስለሆነ።

እኔ ተወያዩ የሚል ቃል እንደኛ የሚስፈራው ማሕበረሰብ ኣይቼ ኣላቅም። ምንድነው ይሄ ሁሉ ኩራት? ምንድነው ይሄ ሁሉ እብሪት? . . . ስለዚህ ቆም ብለን፤ ውይይቱን እንሞክረነው፤ ጦርነቱን እኮ ማንም ኣይወስድብንም። ጦርነቱ የትም ኣይሄድብንም፤ ነገም ከንገ ወዲያም የኛው ነው።

ጦርነቱ እኮ ለ፱ ወር ተደርጓል። በጦርነቱ የምንፈልገውን ኣላገኘንም። የኢትዮጵያ የህልውና ኣደጋ የመፍረስ ኣደጋ የሚለውን እስካሁን እየሰማን ነው። ከ 9 - 10 ወር በኃላ ሕወሓት ቀንሷል? ተዳክሟል?!

. . . እስቲ ለሰላም ዕድል እንስጥ። ጦርነቱ የትም ኣይሄድብንም፤ ነገም ከንገ ወዲያም የኛው ነው"

ጎዳና ያዕቆብ


Amazing speech! There is hope if people pay attention to marvelous people like Godana.