Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

የአውሎ ሚዲያ ዋና አዘጋጅ በቃሉ አላምረው፣ የሚዲያው ተንታኝ ፋኑኤል ክንፉና የኢትዮ ፎረም ጋዜጠኛ አበበ ባዩ በአፋር ክልል አዋሽ ሰባት ኪሎ ከተማ በእስር ናቸው

Post by sarcasm » 14 Aug 2021, 08:26

በእስር ላይ በሚገኙት 3 ጋዜጠኞች ላይ ለአራተኛ ጊዜ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተፈቀደ
ethiopiainsider


በሃሚድ አወል


የአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ ፍርድ ቤት፤ በአፋር ክልል አዋሽ ሰባት ኪሎ ከተማ በእስር ላይ በሚገኙ ሶስት ጋዜጠኞች ላይ ለአራተኛ ጊዜ የምርመራ ጊዜ ፈቀደ። ፍርድ ቤቱ የምርመራ ጊዜውን የፈቀደው የአውሎ ሚዲያ ዋና አዘጋጅ በሆነው በቃሉ አላምረው፣ በሚዲያው ላይ በተንታኝነት በሚሳተፈው ፋኑኤል ክንፉ እንዲሁም የ“ኢትዮ ፎረም” ጋዜጠኛ በሆነው አበበ ባዩ ላይ ነው።

የወረዳው ፍርድ ቤት ለዛሬ ነሐሴ 6፤ 2013 ቀጥሮ የነበረው፤ ፖሊስ ባለፈው ችሎት በተፈቀደለት አስር የምርመራ ቀናት ያከናወናቸውን ተግባራት ለመስማት ነበር። ነገር ግን ፖሊስ “ምርመራዬን አላጠናቀቅኩም” በማለቱ ፍርድ ቤቱ ተጨማሪ አራት የምርመራ ቀናት መፍቀዱን የጋዜጠኞቹ ጠበቃ አቶ ታደለ ገብረመድሀን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።

Continue reading https://ethiopiainsider.com/2021/4197/