Natnael Mekonnen
tSplcSonso5rhed ·
#TPLF : የመቀሌና የሽሬ ጎዳናዎች ለልመና በወጡ ሴቶችና ህፃናት ተጥለቅልቀዋል በተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች ሰሞኑን አስከፊ ርሃብ እያንዣበበ መሆኑን በተለይም ደግሞ በመቀሌና በሽሬ ጎዳናዎች ላይ ለልመና የወጡ ሴቶችና ህፃናት ማሳያ ናቸው፡፡ በሁሉም የትግራይ የመንግስት መዋቅር ያሉ ሰራተኞች ሙሉ በሙሉ ስራ ማቋረጣቸውና ይህን ተከትሎም ወርሃዊ ደሞዝ መከፈል መቆሙ እንዲሁም በከተሞች የገቢ ምንጫቸውን በንግድ ስራና በሌሎችም ዘርፎች ያደረጉ የህብረተሰብ ክፍሎች ገቢ ማግኘት አለመቻላቸው ነዎሪውን ለተመፅዎችነትና በሌሎች እጅ ላይ እንዲወድቅ አድርጓታል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ በመቀሌና በሽሬ ከተሞች ህዝቡ መራቡንና ገንዘብ ያለው እንኳን በገንዘቡ ገዝቶ ሊበላው የሚችለው እንደሌለ፤ ከዚህ ጋር በተያያዘም ሴቶችና ህፃናት በየጎዳናዎች በመውጣት ወደ ዝርፊያና ነጠቃ በስፋት የገቡ መሆኑን፤ አሁን ባለው ሁኔታ አለም አቀፉ ማህብረሰብና የኢትዮጰያ መንግስት እንደምንም ብለው በቀጣይ ሁለት ሶስት ሳምንታት ውስጥ የህዝቡን ህይወት ለማትረፍና ከአስከፊ ረሃብ ለመታደግ አስቸኳይ የምግብ ዕርዳታ ካለደረጉ፤ ህዝቡ ወደ አስከፊ ሁኔታዎች ውስጥ ሊገባ እንደሚችል የውስጥ ምንጮቻችን ከስፍራው አረጋግጠዋል፡፡