Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4487
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

በቀድሞው 31 ክፍለጦር አዛዥ ጀነራል ከበደ ፍቃዱ የሚመራው የትህነግ ሰራዊት ወልዲያ ዙሪያ አፈር በልቱኣል፥ ዜና መከላከያ

Post by Za-Ilmaknun » 13 Aug 2021, 13:33

:mrgreen: :x
ነሀሴ 7 ቀን 2013

በከሃዲው የቀድሞው የ31ኛ ክ/ጦር አዛዥ ብ/ጄ ከበደ ፍቃዱ የሚመራው የጠላት ጦር በወልድያ መግቢያ ጥቁር ውሃ አካባቢ ተደምስሷል ፡፡

በዚህ ውጊያ ከ70 በላይ የጠላት ሃይል ሊደመሰስ ችሏል ፡፡

ጀግኖቹ የ21ኛ ክ/ጦር የሰራዊት አባላት የድል ችቦዋቸውን ከፍ አድረገው እያውለበለቡ በጥቁር ውሃ ላይ ሌላ አዲስ ታሪክ መስራታቸውን ቀጥለዋል።

ክፍለ ጦሩ በጥቁር ውሃ አካባቢ በወገን ጦር ላይ ጥቃት ለማድረስ በእንቅስቃሴ ላይ የነበረውንና በከሃዲው ጀነራል ከበደ ፍቃዱ የሚመራውን የጠላት ጦር በአስደናቂ የወታደራዊ ስልት መደምሰስ መቻሉን የ211ኛ ብርጌድ ዋና አዛዥ እና ም/አዛዥ ለኦፕሬሽናል አስታውቀዋል።

አዛዦቹ እንዳስታወቁት ፣ በሰራዊቱ እልህና ቁጭት አስደናቂ የጀግንነት ተግባር ፈፅመናል ብለዋል።

ክ/ጦሩ በጥቁር ውሃ አካባቢ ለይ በፈፀመው የጀግንነት ውሎው ከ70 በላይ የጠላት ሃይል ሲደመሰስ ፣ 19 ክላሽን ኮቭ መሣሪያ ፣ 5 ስናይፐር እና በርካታ ቁጥር ያላቸው ከከባድ እስከ ቀላል የጦር መሳሪያዎች ተማርከዋል ።

ሠራዊቱ አሁንም የህልውና ዘመቻውን በአስተማማኝ የጀግንነት መንፈስ ለመወጣት ከመቸውም ግዜ በላይ ዝግጁ መሆኑንም አረጋግጠዋል።

መብራቱ አራርሶ
ፎቶግራፍ ማርቆሥ አለሙ


Post Reply