ፋሲል የኔአለም ያጋለጠውን የውታፍ ነቃዮች አሳፍሪነት ተመልከቱ!!
Fasil Yenealem
ህወሃቶች አንድ መቶ አለቃ ቢማርኩ፣ የሻለቅነት ማዕረግ ሰጥተውት መቶ ጊዜ ፕሮፕጋንዳ ይሰሩበታል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሌ/ ኮሎኔል የሚያክል ማዕረግ ያለው ሰው ማርኮ እንደ ተራ ሚሊሺያ በቲቪ ያሳየዋል። በዚህ አይነት ስንቱ ኮሎኔልና ሻለቃ ተማርኮ ይሆን?
ይህ ከአራት ቀናት በፊት በተላለፈው የ ኢቲቪ ዜና ላይ አንገቱን ደፍቶ የሚታየው ሰው ሌ/ኮ አማኑኤል አብርሃ ይባላል። በቅርብ የሚያውቁት ሰዎች እንደነገሩኝ በቀድሞ ሜቴክ ፖዎር ኢንዱስትሪ ም/ ስራ አስኪያጅ (ኦፕሬሽን ሃላፊ) ነበር።
ግለሰቡ ከህዳሴ ፣ ስኳርና ማዳበሪያ እና ሌሎች በርካታ ፕሮጀክት ጋር በተያያዘ ዝርፊያ የፈጸመ ሰው መሆኑን እሱን በቅርብ የሚያውቁ ሰዎች ይናገራሉ። መንግስት ይሄን ሰዉ እንደተራ ታጣቂ አይቶ በተሃድሶ ስም እንዳይፈታዉ አቤት እንድልላቸውም ጠይቀውኛል። ጥያቄያቸውን በአደባባይ አቅርቤያለሁ።
Please wait, video is loading...
Fasil Yenealem
እንደገና ሌላ ጉድ። ከ ሌ/ኮሎኔል አማኑኤል አብርሃ ጀርባ የተቀመጠው ደግሞ ሽበታሙ ሰው ሌ/ ኮሎኔል ገብረመስቀል ነው። ሜቴክ ፓወር ኢንዱስትሪ ውስጥ የቤቶች ጉዳይ ክትትል ኃላፊ የነበረ ነው።
ሌ/ኮ አማኑኤል ምክትል ሳይሆን ዋና ስራስኪያጅ ነበር። ትራንስፎርመር እንሰራለን ብሎ አገሪቱን ያራቆተ ከክንፈ ዳኘው ቀጥሎ ያለ ሰው ነበር። መንግስት ሆይ እባክህ የመረጃና ደህንነት መዋቅርህን ፈትሽ፤ አሳ ነባሪ ይዘህ፣ ቤዞ አሳ እንደያዝክ አትተውን።
Please wait, video is loading...