By Ras Robiso Dengora
የወያኔ ዋናዎቹ ሁለቱ የጦርነት ስልቶች ፦
1. ብዙ ሰው የመማገድ ስልት( 'Human wave ' technique )
ደርግ ጋር ከነበረው ጦርነት ጀምሮ ኢትዮ ኤርትራ ላይ አሁን ደግሞ በስፋት አፋር፣ ወልቃይት፣ ሰሜን ወሎ ግንባር እየተጠቀሙ ያሉት ጨካኝ ስልት ነው። በነዚህ ግንባር እንደተሰማው የመጀመሪያ ተዋጊዎች ሲያልቁ ሌሎች ህፃናት፣ አረጋውያን ፣ ሴቶች ሳይቀሩ አምጥተው ይማግዷቸዋል። አንድ ግንባር ያለ የወገን ጦር ወንድም ሲነግረኝ "መግደል ራሱ ያደክማል" በሚል ነው የገለፀው። እነ ጀነራል ፃድቃንና ጓደኞቹ እቅድ እስከ 2 ሚሊዮን ሰው ገብሮ ማሸነፍ ነው የሚል እንደሆነ እቅዱን ስሰማ በእነዚህ ሰዎች ክፋት ሰይጣን ራሱ እንዴት እንደሚቀና ነው ያሰብኩት። ለጥቂት ግለሰቦች የወንበር ጥማት ሲባል የደሀ ገበሬ ልጅ እንደ እንጨት ለጦርነት መማገድ ምን የሚሉት ስልት እንደሆነና በዚህ መንገድ ቢያሸንፉ እንኳን ምን ያህል የትውልድ ክፍተት ህዝቡ ላይ ጥለው እንደሚያልፉ አንድ ግዜ እንኳን ቆመው አለማሰባቸው ያሳዝናል።
2. የተለያዩ ፕሮፖጋንዳዎች፦
ወያኔ በራሳቸው ( ጌታቸው፣ ስታሊን፣ አሉላ፣ ዘፀአት ...) ከሚመራው ቀጥተኛ ፕሮፖጋንዳ ተጨማሪ የተለያዩ ስልቶችን እንደሚጠቀም ተደርሶበታል ከነዚህም ውስጥ፦
ሀ. በጦርነቱ መሀል የማረኳቸውን መከላከያዎችና የራሳቸውን ግለሰቦች የመከላከያ ልብስ በማልበስ ወደ አልተያዙ ከተሞች ሰርገው እንዲገቡና ከተማውን በተለያዩ ወሬዎች እንዲያሸብሩ ማድረግ ፦
መሪዎቻችን ስለሸጡን ተበተንን።
ከባድ ሀይል እየመጣ ስለሆነ ከተማውን ጥላችሁ ውጡ።
የሚሉ የውሸት ወሬዎችን ይነዛሉ የከተማው ሰው ነቅሎ ይወጣል በቀላሉ ይቆጣጠራሉ። ለዚህ ምሳሌ የሚሆኑት አዲርቃይና ቆቦ ዋናዎቹ ናቸው።
ለ. በተለያዩ ጥቅማጥቅም የተገዙ የራሳችን ባንዳዎችን የሚታገለው ሰው መሀል በመጨመር እንዲሁም ከውጭ በማህበራዊ ሚዲያ ስልታዊ ሽፋን በመስጠት፤ ከተለያዩ ከተሞች ወደ ትግሉ ሜዳ ስልክ በመደወልና ተስፋ አስቆራጭ ዜናዎችን በመንገር፤ መከላከያው ከድቶናል፤ አመራሩ ፈርጥጧል የሚሉ የተለያዩ የውሸት ወሬዎችን በመንገር እያጠቃ የነበረውን ሀይል ሁሉ ወደኋላ እንዲያፈገፍግ ብዙ ቆሻሻ ስራ ተሰርቷል።
ሐ. የአማራ ልዩ ሀይል፣ የመከላከያ ልብስ የራሳቸውን ወታደር በማልበስና በቆረጣ በመውጣት በተለይ ፋኖና ሚኒሻውን እንደወጉት ማስመሰልና በውሸት ወሬ ጦሩ እንዲፈታ ማድረግ። ...
በገቡባቸው ከተሞች በደንብ እስኪቆጣጠሩ እኛ ፀባችን ከአብይ ጋር እንጅ ከእናንተ ጋር አይደለም።( ውለው ሲያድሩ ግን መርፌ ሳይቀር ማህበረሰቡን ዘርፈውታል ... የተለያዩ ግለሰቦች አንዳንድ ቦታ የአይምሮ በሽተኞችን ጭምር ገለዋል ... )
ስለዚህ ወገኔ ሆይ ይህ ጦርነት ልብህን ለሁለት የሚከፍል ነገሮችን በጭራሽ አትስማ ። እየገጠምክ ያለኸው ከዚህ በፊት "አማራውን አከርካሪውን ሰብረን ቀብረነዋል" ሲልህ ከነበረው አረመኔው ህወሓት ጋር ሲሆን ዛሬም በተደጋጋሚ በጌታቸው ረዳ በኩል እንደተናገሩት "ጦርነቱ የአማራው elite ( የነቃው ነጋዴ፣ የተማረ አማራ፣ የሀይማኖት አባት፣ ጎበዝ ገበሬዎችን... ) ጋር ሂሳብ ማወራረድ ነው" በተደጋጋሚ የተለያዩ ሚዲያዎች ላይ ሲል ሰምተሀልና ይልንን ያለህን ሀይል በልተኸው ለመቀደስ የምትችል መከላከያውን ተቀላቀል ይህ ካልሆነ የአማራ ልዩ ሀይልን ይህ ካልሆነልህ በሎጅስቲክና በፕሮፖጋንዳ አግዝ...እነዚህ ካልሆኑልህ ቢያንስ ለጠላት መጠቀሚያ አትሁን አርፈህ ተቀመጥ።
Photos of Dead Tigrayan/TPLF child soldiers!!
Tigrayans leader Genaral Tsidkan Gebretensae is doing as he promised!!



