Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4487
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

አሁን ለድርድር ዝግጁ ነን እያለ ነው ጌታቸው ረዳ። ቶክስ አቁም ሲነሳ!

Post by Za-Ilmaknun » 11 Aug 2021, 19:09

<<አሁን ለድርድር ዝግጁ ነን>> ብሏል የጁንታው ተላላኪ

👉 ጌች አሁን መግለጫ እየሰጠ ነው በመግለጫውም አሁን ለድርድር ዝግጁ ነን፣የቱርክ መንግስት ለመንግስት መሳርያ እያሰገባ ነው የኤርትራ መንግስት ዳግም ሊወረን ተዘጋጅቷል እያለ ነው።

[ኤ.ኤፍ.ፒ]:- በትላንትናው እለት የኢትዪጲያ መንግስት ለአንድ ወር የቆየውን የተኩስ አቁም ውሳኔውን በማንሳት ጦርነት ሊጀምር እንደሆነ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅ/ቤት አማካኝነት ገልፇል እና በዚህ የመንግስት ውሳኔ ላይ ያላችሁ አቋም ምንድነው? ??

👉የናንተስ ውሳኔ ???

[ጌታቸው ረዳ] :- በመጀመሪያ ተኩስ አቁም የሚባለው ጨዋታ ነው። 8 ወር ሙሉ ተደብድበናል ፣ ተወረናል ፣ ባጠቃላይ ትልቅ ጉዳት ነው የደረሰብን ።

👉 ነገር ግን አፈር ልሰን በሚባል ደረጃ እንደገና አገግመን ስንጠናከር ወዲያው አብይ አህመድ ተኩስ አቁሚያለሁ አለ ። ወደ ጥያቄው መልስ ስገባ የአብይ ውሳኔ የሚጠበቅ ነው ።ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ 2 ክልሎችን በጥቂት ቀናት ውስጥ ተቆጣጥረናል። ይህ አስደንግጦት ነው ለዳግም ጦርነት እየቀሰቀሰ ያለው። የኛ ውሳኔ በተቻለን አቅም እንታገላለን ነው ባጭሩ🤣

[ኤ.ኤፍ.ፒ]:- በሰሞኑ ጦርነት በተለይ በአፋር ክልል በናንተ ሀይሎች ከ250 በላይ ህፃናት እና ሴቶች ፣ስደተኞች ጥቃት ደርሶባቸው እንደሞቱ መንግስት እየገለፀ ነው ።በዚህ ጉዳይ ያለዎት አስተያየት ምንድነው?

👉[ጌታቸው ረዳ]:- በአፋር ግንባር የተከሰተው ድርጊት እንደ ግለሰብ እኔንም አሳዝኖኛል ። ግን በጦርነት መካከል ንፁሃን ይጎዳሉ ይህ ግን መከሰት አልነበረበትም ። በአፋር ግንባር ድል ብንቀናጅም በርካታ የኛም ተዋጊዎች መስዋት ሆነዋል። ብዙ ሀይል በዛ ግንባር ነው ሉዝ ያደረግነው ግን እጅ ሳንሰጥ እየታገልን ነው

[ኤ.ኤፍ.ፒ]:- በትግራይ ክልል ድጋሚ ጦርነት ተቀስቅሶ የባለፈውን አይነት እልቂት እና ኪሳራ ከመድረሱ በፊት ለምንድነው ከፌድራል ከመንግስት ጋር በድርድር ችግሩን ለመፍታት ያልተሳካላችሁ ?

👉[ጌታቸው ረዳ]:- በኛ በኩል ከበቂ በላይ ጥረት አድርገናል ከዚህ ቀደም ያወጣነው ባለሰባት ነጥብ አቋም እንዳለሆኖ አሻሽለን ያስማማል ፣ ያደራድራል ብለን ያሰብነውን መደራደሪያ አቅርበናል። 🤣ለአለም አቀፉ ማህበረሰብም እንዲያደራድረን ተማፅነናል። አሁንም እያልን ያለነው " ቅድሚያ እንደራደር ፣ ግጭት ለረዥም አመታት አይተነዋል ፣ ኪሳራ እንጂ ትርፍ የለውም"ብለን ለመንግስት ገልፀናል። ነገር ግን አብይ እኛ ካልጠፋን እንቅልፍ አልወስድ ብሎት የህወሀት ሀይልን ለማጥፋት ለ120 ሚሊዮን ህዝብ ጥሪ አድርጎ ይሄው በትላንተናው እለት ብቻ በርካታ ከባድ መሳሪያዎችን እያስጠጋ ነው።

[ኤ.ኤፍ.ፒ]:- በአሁን ወቅት የሰብአዊ እርዳታ እየገባነው? ?

👉[ጌታቸው ረዳ]:- መንግስት መቐለን በተቆጣጠረ ጊዜ የገቡ የነበሩ የተወሱ እርዳታ ምግቦች አሉ ።እንዲሁም ከሰሞኑ በአፋር በኩል የገቡ ከ400 በላይ መኪኖች እርዳታ አለ። ነገር ግን ይህ በቂ አይደለም ። በርካታ ህዝብ አሁንም የርሀብ ስጋት ላይ ነው 😂

Via አሁን አየ አይኔ

[ኤ.ኤፍ.ፒ]:- ወደ ኤርትራ እንሂድ, የኤርትራ መንግስት ጋርስ ለመደራደር አላሰባችሁም? ? ማለት ኤርትራም ጋር ከባድ ፈጥጫ ላይ ስላላችሁ

👉[ጌታቸው ረዳ]:- የሻእቢያ መንግስት ለስሙ መንግስት ይሁን እንጅ ኢሳያስን የሚያዘው አብይ ነው። አብይ ኢሳያስን ውረር ካለው ይወራል። የጋራ ጠላት ያገናኛቸው ስለሆኑ። ከሻእቢያ መንግስት ጋር ለመወያየት አይታሰብም ።

via Tesfaye Kebede


Post Reply