------
ጦርነት ከውድመት፣ ከእልቂትና ከህዝብ መናፈቀል በስተቀር ሀገራችን ለገባችበት ችግር መፍትሔ ሊሆን አይችልም። ይልቁንም በህዝቦቻችን መካከል ቂም በቀልን ዘርቶ እስከዛሬ ድረስ ያላየነው መከራ ውስጥ ሊከተን ይችላል። ህዝቡ ለራሱ በኑሮ ውድነት እየተሰቃየ ነው። ለዚህ ህዝብ ጦርነትን መመኘት በእከክ ላይ ጠኔን እንደመሸመት ነው።
ኢትዮጵያችን የሚያስፈልጋት ሰላም፣ መረጋጋት፣ ስራ፣ ልማት፣ ኢንቨስትመንት፣ ዕድገትና ብልፅግና ነው እንጂ ጦርነት አይደለም። ስለዚህ ለሀገሩ የሚጨነቅ ሰው ሁሉ በዚህ ላይ ቆም ብሎ ሊያስብ ይገባል።
------
አሁንም እንላችኋለን!!
ሁለቱም ሃይሎች ጦርነቱን እንዲያቆሙና በመካከላቸው ያለውን ችግር በውይይት፣ በንግግር፣ በድርድር እና በውይይት እንዲፈቱት በኢትዮጵያ ህዝቦች ስም እንለምናቸዋለን። የሀገር ሽማግሌዎች፣ ባህላዊ መሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሰላም ሰባኪዎች፣ የሲቪክ ተቋማት መሪዎች፣ ታዋቂ ምሁራን ዝምታችሁን ሰብራችሁ ሁለቱ ሃይሎች ውይይት እንዲጀምሩ በሚደረገው ጥረት ውስጥ ሃላፊነታችሁን እንድትወጡ እንጠይቃችኋለን።
------
አላህ ሰላሙን ያውርድልን!!
አሚን! አሚን! አሚን!
Please wait, video is loading...
