መቆሚያችን መረብ ወንዝ ብቻ ነው!
Posted: 10 Aug 2021, 13:16
ከፍተኛ ምት የደረሰበት ወያኔ በአፈ ቀላጤው በኩል ደቡብ ጎንደርን እየሸነሸነው ነው ብሎ ፅፏል አሉ። መሸንሸን ምን እንደሆነ በትናንትናው እለት የኢትዮጵያ ህዝባዊ ኃይል አሳይቶታል። እነዚህ ሰዎች ጦርነት ምን ማለት እንደሆነ ትናንት በነበረው ውሎ ተረድተዋል። በእርግጠኝነት የምንናገረው ይህ ቦታ የወያኔ መቀበሪያ እንደሚሆን ነው። ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት ወንበዴ ቡድን ያለ የሌለ ኃይሉን አሰባስቦ በተደጋጋሚ ቢሞክርም አልተሳካለትም። በወገን ጦር በኩል የደረሰ ጉዳት እዚህ ግባ አይባልም። ቀላል ቁስለት ብቻ ተመዝግቧል። በተቃራኒው ያለው ወንበዴ እየበረረ የመጣው ሁሉ በወገን ጦር ቅንጅት በመቄት ተራሮች ስር ተደፍቶ እንዲቀር አድርጎታል።
የመከላከያ ተጋድሎ የሚደንቅ ነበር። ኮማንዶው ይዋጋል አይገልፀውም። የልዩ ኃይላችን ትብብር ግሩም ነው። ፋኖ ጦርነትን ይሰረዋል ማለት ይቻላል። ህዝባዊ ኃይሉ የሚደንቅ ተጋድሎ አድርጓል። ቁስለኛ በማግለል፣ ምግብ በማቅረብ የአካበቢው ህዝብ ያሳዬው መሯሯጥ ታሪካዊ ነበር። የደቡብ ጎንደር ዞን እና የአካባቢው አስተዳደር፣ ከክልል የመጡ አመራሮች ያሳዩት አመራርነት የሚያስመሰግን ነው። ታሪክ የማይረሳው መናበብ እና ተጋድሎ ተደርጓል። ዛሬም እየፈረጠጠ ያለውን የወያኔ ኃይል የወገን ጦር ከኋላ ደርሶ እያካለበው ነው። መቆሚያችን መረብ ወንዝ ብቻ ይሆናል...!
ጋሻው መርሻ