ሰበር ዜና: ከደሴ ከተማ አስተደደር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ የተሰጠ መግለጫ።
Posted: 10 Aug 2021, 08:46
የደሴ ከተማ አስተዳደር ወቅታዊውን የጠላት እንቅስቃሴ መሠረት በማድረግ በርካታ ስራዎችን ሲሰራ የቆየ መሆኑ ይታወቃል።
ነባራዊው የከተማችን ሁኔታ ከወትሮው በተለየ የከተማችንን ህዝብ ልዩ ክትትልና ድጋፍ የሚጠይቅ ነው።
በከተማችን ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተፈናቃይ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ የሀይማኖት ተቋማትን ጨምሮ ከልዩ ልዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሠራት ላይ ይገኛል።
ሆኖም ከተማችን በጠላት ስለተከበበ እና ለከተማችን ህዝብ ሁለንተናዊ ደህንነት ሲባል በሰዓት የተገደበ የተሽከርካሪና የሰው የእንቅስቃሴ ገደብ ተቀምጧል።
1ኛ. መላ የከተማችን ነዋሪዎች ከምሽቱ 2:00 ጀምሮ ከተፈቀደላቸው የፀጥታ አካላት ውጭ የትኛውም ዓይነት እንቅስቃሴ የተከለከለ ነው።
2ኛ.ከተፈቀደላቸው የፀጥታ ተቋማትና የጤና ተቋማት ተሽከርካሪዎች ውጭ ከምሽቱ 2:00 ሰዓት ጀምሮ እንቅስቃሴአቸው እንዲገደብ ተወስኗል።
3ኛ. የሶስት እግር ባጃጅ ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ እስከ ምሽቱ 12:00 ሰዓት ብቻ እንዲሆን የተወሰነ መሆኑን እናሳውቃለን።
ይህ ውሳኔ ከዛሬ ነሀሴ 04/2013 ዓ.ም ጀምሮ በከተማችን ተግባራዊ ይደረጋል። መላ የከተማችን ነዋሪዎችም በተለመደው አግባብ ለሁሉን አቀፍ ትብብር እራሳችሁን ታዘጋጁ ዘንድ የደሴ ከተማ አስተዳደር ጥሪውን አቅርቧል።

ግልባጭ ለአዳነች አቤቤ : - የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤትም ከአሁኑ ቢዘጋጅ ይሻለዋል ::