******************
ህዝብ ላይ ክህደት ፈፅማችሁ ለመደራደር አስባችሁ ከሆነ ከሃዲ የከዳውን ህዝብ ወክሎ ሊደራደር እንደማይችል እወቁት።
****************
የአብይ አህመድ መንግሥት በፋና በኩል በእኩለ ሌሊት እነ ደብረጽዮን ፃድቅ ናቸው የሚል ሃተታ ጽፏል። ጉድና ጅራት ከበስተኋላ ነው እንዲሉ የአብይ አህመድ መንግሥት ከህወሓት ጋር ለመደራደር ደብረጽዮን ፣ ሞንጆሪኖ፣ አለም ገብረዋህድ የመሳሰሉት የትግራይ ክልል መንግሥት ተወካይ ነን የሚሉት አካላት ጻድቅ ናቸው የሚል ዜና ጽፎ ለውታፍ ነቃዩ እንዲያራግብ በእኩለ ሌሊት ትዕዛዝ ተሰጥቷል።
ከሳምንት በፊት ጀነራል ጻድቃን የተሻለ ነው መደራደር ይፈልጋል የሚል እነ ደብረጽዮንን የሚወነጅል ዜና ሲያራግቡ የነበሩ የመንግሥት አፈቀላጤዎች ዛሬ ደግሞ ተገልብጠው እነ ደብረጽዮን ያማልዳሉ እያሉ ነው።
ነገ ደግሞ ልንደራደር ተቀምጠናል እነ ደብረጽዮን የሰሜን እዝ በማጥቃታቸው ተፀፅተዋል የሚል ዜና ያመጡልን ይሆናል። ተለማመዱት እያሉን ነው። ለማንኛውም ፈፅሞ ባልተለመደ ሁኔታ በእኩለ ለሊት ይሄንን ለመጻፍ የተገደዱት ለምን ይሆን ? የጓሮው የድርድር ቁማር ሳይጋለጥ እንቅደም ነገሩን በሌላ መንገድ አለስልሰን እናቅርብና ህዝቡ እንዳይቆጣ እናድርግ የሚል ስልት መሆኑ ነው ? እቺን ጫወታ ብትገፉባት ከእኩለ ሌሊት ቅዠት ወደ እኩለ ቀን እብደት እንደሚያሻግራችሁ እወቁት።
ህዝብ ላይ ክህደት ፈፅማችሁ ለመደራደር አስባችሁ ከሆነ ከሃዲ የከዳውን ህዝብ ወክሎ ሊደራደር እንደማይችል እወቁት።
Please wait, video is loading...