Page 1 of 1

ለህወሓት ለምን ታሽቃብጣለህ ላላችሁኝ ፡-

Posted: 07 Aug 2021, 08:32
by sarcasm
ለህወሓት ለምን ታሽቃብጣለህ ላላችሁኝ ፡-

By Bati Post - ባቲ ፖስት
.
የፌደራሉ መንግስት እንዳለው የጦርነቱ መነሻ የሰሜን እዝ ላይ በተቃጣው ጥቃት እንደሆነ በተደጋጋሚ ተናግሯል። ነገር ግን መንግስት ጉዳዩ በገለልተኛ ወገን እንዲጣራ ፈቃደኛ አይደለም። የተጨበጠ ማስረጃም እስካሁን አልቀረቡም። የአፍሪካ ህብረት በራሴ መንገድ አጣርቻለው ብሎ ያወጣው መረጃ ደግሞ የጦርነቱ ተንኳሽ የፌደራሉ መንግስት ነው ብሏል።
,
ለምሳሌ የጦርነቱ ተንኳሽ ህወሃት ናት እንበል። የመንግስትን የህግ ማስከበር ዘመቻውን በአስገዳጅ ሁኔታ የተደረገ ነው ብለን ጦርነቱን ደገፍን እንበል!! የኤርትራ ወታደር ገብቶ የትግራይ ህዝብን መጨፍጨፉን፣ ንፁሀንን መረሸናቸውን፣ ሴቶች መደፈራቸውን፣ የከተማዎችን መሰረተ ልማቶች ማውደማቸውን፣ የአማራ ክልል የትግራይ መሬት መዝረፉን፣ ወራሪው ሻቢያ የትግራይ ህዝብን መሬት መዝረፉን፣ ሚሊየን ህፃናት መራባቸውን፣ የትግራይ ህዝብ ንብረቶች መዘረፋቸውን፣ ድሮንን ጨምሮ በከባድ መሳሪያዎች ትግራይ መደብደቧን ...ወዘተ በየትኛው አግባብ ነው የምደግፈው??
,
የትግራይ ህዝብ የተፈፀመበትን በደል ለመቀልበስ የሚያደርገውን ማንኛውም አይነት ጥረትን ለምን እቃወማለሁ?? የአማራ ክልል የትግራይ መሬትን ሲዘርፍ አግባብ ሆኖ TDF ደግሞ የተወሰደውን መሬታቸውን ሲያስመልስ ህገወጥ ሊሆን አይችልም። የፌደራሉ መንግስት ትግራይ ውስጥ ገብቶ ያሻውን ሲያደርግ "ህግ እያስከበረ ነው" እየተባለ TDF ደግሞ ለተፈፀሙ በደሎች "ሂሳብ እናወራርዳለን" ብሎ ስለተንቀሳቀሰ ህገወጥ ሊሆን አይችልም።
,
ከጦርነት በኃላ ቀውሱ በድርድር ቢጠናቀቅ ጥሩ ነበር። ድርድር ከሌለ ግን ወራሪውን ማዳከም ዘላቂ መፍትኔ ከማበጀት አንፃር አስፈላጊ ነው። የTDF ዘመቻም ይኸው ነው። ወራሪ ዳግመኛ እንዳይነሳ እግሩን ትሰብረዋለህ። አለበለዚያ መመለሱ አይቀርም። ይህ የትኛውም የአለም ሀገራት የሚተገብሩት ስልት ነው። ድርድር ከሌለ በተቻለ መጠን የእራስን ሀይልን ማደራጀት እና የባላንጣን አቅም ደግሞ ማዳከም የተለመደ ነው።
,
እኔ የ TDF ዘመቻን የምመለከተው ከዚህ አንፃር ነው። በጠላት ተከበው ማልቀስን አልመረጡም። እየተደበደቡ "ማሩን" ብለው መጮህ አልፈለጉም። ዘግናኝ ግፍ ተፈፅሞባቸው በሀዘን መማቀቅን አልመረጡም። ይልቅ ወድቀው ተነስተዋል። ቆስለው ድነዋል። ሀዘናቸውን ውጠው የመጣባቸውን ሁሉ መክተዋል። በጠላቶቻቸው ላይ አንድ ሆነዋል። የፌደራሉ መንግስት "ህግ አስከብራለሁ" ብሎ ወደ ህገወጥነት ሲቀየር እነሱም በተራቸው ህገወጥነት እንዴት እንደሚቀለበስ በሚገባው ቋንቋ እያሳዩት ነው። ይህንን በማድረጋቸው እደንቃቸዋለው!
.
ፁሁፌን ሳጠቃልለው - "ህግ ማስከበር" ተብሎ በትግራይ ህዝብ ላይ የተፈፀመው በደል ብቻውን ከትግራይ ህዝብ (TDF) ጋር እንድቆም ያደርገኛል። ይኸው ነው!
.
- ፍንፊኔ ታይምስ
Please wait, video is loading...


Tarikayew Geses
ሰው እንዲህ ገብቶት ሲፅፍ ደስ ይላል በእውቀት ላይ የተመሰረተ አገላለፅ ተባረክ