Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
tarik
Senior Member+
Posts: 37207
Joined: 26 Feb 2016, 13:04

አቶ ግዛቸው ሙሉነህ: ላሊበላ የገባው የህወሓት ሽብር ቡድን አሁን ላይ በመከላከያ ሰራዊትና በክልሉ ልዩ ሃይል እየተመከተ ነው(((WHY U LET THEM IN)))?!!! WEEY GUUD !!!

Post by tarik » 06 Aug 2021, 07:27

Natnael Mekonnen
taS1pocnhsoredf ·
ላሊበላ የገባው የህወሓት ሽብር ቡድን አሁን ላይ በመከላከያ ሰራዊትና በክልሉ ልዩ ሃይል እየተመከተ ነው" - አቶ ግዛቸው ሙሉነህ

#Ethiopia : በትላትናው ዕለት የህወሓት ታጣቂዎች አማራ ክልል ወደምትገኘው ላሊበላ ከተማ መግባታቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች እንዲሁም የከተማይቱ ምክትል ከንቲባ አቶ ማንደፍሮ ታደሰ ማረጋገጣቸው ይታወቃል።

የቡድኑ ታጣቂዎች በሶስት ትምህርት ቤቶች ውስጥም ካንፕ ሰርተው መቀመጣቸውን ነዋሪዎች እንደገለፁ አይዘነጋም።

ላሊበላ ካለው ሁኔታ ጋር በተያያዘ በዛሬው ዕለት የአማራ ክልል ኮሚኒኬሽን ኃላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ተናግረዋል።

ላሊበላ የገባው የህወሓት ቡድን አሁን ላይ በመከላከያ ሰራዊትና በክልሉ ልዩ ሃይል እየተመከተ ነው ብለዋል አቶ ግዛቸው ሙሉነህ።

ህብረተሰቡ በቡድኑ የሃሰት ፕሮፓጋንዳ አካባቢውን ለቆ መውጣት እንደሌለበት የገለፁት አቶ ግዛቸው "ህብረተሰቡ ሳይሸበር ራሱን ሊከላከልና አካባቢውን በንቃት ሊጠብቅ ይገባል" ብለዋል።

ህወሓት አሁን ላይ በክልሉ 3 ግንባሮች ውጊያ መክፈቱን አቶ ግዛቸው የገለፁ ሲሆን አሁን ላይ በሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ ልዩ ሃይል ፣ በፋኖ እየተደመሰሰ እና እየተመታ ነው ብለዋል።

ዳይሬክተሩ በርካታ የቡድኑ አባላት መማረካቸውን መጥቀሳቸውን ኤፍ ቢ ሲ በድረገፁ አስነብቧል::