እንቆቅልሽ
Posted: 31 Jul 2021, 09:28
ስታጪ ልመና፣ ስታገኚ ሸረኛ
ሲቀርቡሽ ግፈኛ፣ ሲርቁሽ ቂመኛ
ሲኖርሽ ደመኛ፣ ስታጪ ቀማኛ
ሲያጎርሱሽ ተናካሽ፣ ሲረሱሽ ተካሳሽ
ፍቅር የማያውቅሽ፣ እርጉም አንቺ ማነሽ?
ድርቅ ብለሽ፣ ጥውልግ ብለሽ
ተፈጥሮ በድሎሽ፣ በዝቶ ክፋትሽ
እግዚኦ ማለት፣ እንዴት ተሳነሽ?
ሲቀርቡሽ ግፈኛ፣ ሲርቁሽ ቂመኛ
ሲኖርሽ ደመኛ፣ ስታጪ ቀማኛ
ሲያጎርሱሽ ተናካሽ፣ ሲረሱሽ ተካሳሽ
ፍቅር የማያውቅሽ፣ እርጉም አንቺ ማነሽ?
ድርቅ ብለሽ፣ ጥውልግ ብለሽ
ተፈጥሮ በድሎሽ፣ በዝቶ ክፋትሽ
እግዚኦ ማለት፣ እንዴት ተሳነሽ?